የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
Addis Ababa City Council (የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጽ/ቤቱ የሚያስፈልጉ ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የጨረታ ሎቶች በግልጽ ጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል፡፡
ሎት 1. ባለ 3 እና 5 ኮከብ ሆቴል
ሎት 2. ለኩነት ዝግጅት የሚያስፈልጉ እቃዎች
ሎት 3. የህትመት አይነቶች
ሎት 4. የፕሮቶኮል ልብስ
ሎት 5. ኃይላንድ ውሃ
ሎት 6. የተለያዩ የመኪና ጎማ እና ዲኮር ዓይነቶች
ሎት 7. ICT እቃዎች
ሎት 8. የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለሞች
ሎት 9. የፅሕፈት መሳሪያዎች
ሎት 10. ፈርኒቸር
ሎት 11. የወንበር ልብስ
በጨረታ ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 400 በመክፈል ሰነዱን ከግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 107 1ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቼክ ወይንም በባንክ CPO 2% ከአጠቃላይ ዋጋ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 10% (አሥር በመቶ) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ የተሰማሩበትን በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የምዝገባ የምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሰነድ ማያያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ በኮፒውና በኦሪጅናል በየገጹ ማህተም መደረግ አለበት፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- በሎት 5፣ በሎት 6፣ ሎት 7 ቁጥር 10 ያለውን እቃ፣ ሎት 8፣ ሎት 9 እና ሎት 10 የምትወዳደሩባቸውን ናሙና መቅረብ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አገልግሎት ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡ ለሎት 4 የህትመት ዓይነቶች ለምትሳተፉት ጥራታቸውና የቴክኖሎጂ ደረጃቸውን የጠበቁ በአጭር ሰዓት ውስጥ መድረስ የሚችል የህትመትና የማስታወቂያ ስራዎች ለመስራታቸው ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ5፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ሲቀር መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑ፤
- መ/ቤቱ ከተገኘው ዋጋ ሳይቀይር እስከ 20% መቀነስ ወይም መጨመር የሚችል መሆኑን፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
አድራሻ፡- ካሳንቺስ ልማት ባንክ ጀርባ ደሱ ተፈራ ህንፃ
ስልክ ቁ. 011 470 6464 ይደውሉ
የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፣
የዘመኑ ግብር የተከፈለበት፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የቫት ተመዝጋቢ የምሥክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
በሎት 1 የሚወዳደሩ በሥራ ዘርፉ ለመሰማራታቸው የብቃት መረጋገጫ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት
