በቂ/ክ/ከ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡-1.የደንብ ልብሶች 2.የጽዳት እቃዎች 3.የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች 4.እድሳት እና ጥገና 5 ህትመት 6.ቋሚ እቃ 7 እድሳት እቃዎች። በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በቂ/ክ/ከ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂ/ክ/ከ የቂርቆስ ጤና ጣቢያ ለ2019 ዓ/ም ለተቋሙ የሚያስፈልጉ፡-1.የደንብ ልብሶች 2.የጽዳት እቃዎች 3.የተለያዩ የጽህፈት እቃዎች 4.እድሳት እና ጥገና 5 ህትመት 6.ቋሚ እቃ 7 እድሳት እቃዎች። በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ሚሟላት የሚችል ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ድርጅት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በጤና ጣቢያው ቅጥር ጊ.ቢ. 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 በስራ ሰአት በመቅረብ እና በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል እና የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ በመውሰድ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ጨረታው በ10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ11:30 ተዘግቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::
ተጫራቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች:-
- በግብር ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ መያዣ የሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ፐርሰንት) በጤና ጣቢያው ስም በተዘጋጀ ሲፒኦ (CPO) ኮፒው ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል::
- ለጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት አስፈላጊውን የትብብር ደብዳቤ ለማወዳደር የሚከፈተው ፖስታ ማለትም በኮፒው ውስጥ በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው::
- አሸናፊው የንግድ ድርጅት የጠቅላላ ዋጋውን 10% በሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅበታል።
- ኦርጅናል ፖስታ በጨረታ ማወዳደሪያ ወቅት አይከፈትም::
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ድረገፅ ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዝርዝር ጤና ጣቢያው ባቀረበው የዋጋ ሰንጠረዥ ላይ በመሙላት እና እያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋጋውን እና ኮፒውን በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው። በተጨማሪም ቴክኒካል ሰነድ ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ተሞልቶ በድጋሚ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለበት።
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ሁሉም ተጫራቾች ናሙና ከጨረታው ሰነድ በጋራ ማቅረብ አለባቸው::
- ለጨረታ የሚቀርቡ እቃዎች ጥራታቸውንና ደረጃቸውን የጠበቀ መሆን አለባቸው::
- ማንኛውም ተጫራች መወዳደር የሚችለው ከንግድ ፈቃድ ጋር ተያያዥነት ባላቸው አቅርቦቶች/አገልግሎቶች ላይ ብቻ ነው::
ማሳሰቢያ:- ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉበሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። የሚቀርቡት ዋጋዎች ተጨማሪ እሴት ታክስን/ተርንኦቨር ታክስን ያካተቱ መሆን አለባቸው::
አድራሻ:- ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከገነት ሆቴል ወደ ሽመልስ ሀብቴ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሚያስገባው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ነው::
