Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)
  • Address ልደታ ክፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ/የኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ጫፌ አናኒ ህንጻ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-8340-636
  • Website
  • Deadline10 Jul 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-07-10 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Used Items

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በዞንና ወረዳ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረት (እስክራፕ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency (የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ)


 

ግልጽ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- 15/2017

 

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ንብረትነቱ የተለያዩ የኦሮሚያ መ/ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ የሆኑ በዞንና ወረዳ ደረጃ የሚገኙ የተለያዩ ብረታ ብረት (እስክራፕ) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ ሲሆን፤

  1. የኤጀንሲው አድራሻ፡- አዲስ አበባ ልደታ ከፍለ ከተማ ባልቻ ሆስፒታል ጀርባ /የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት/ ጫፌ እናኒ ህንጻ ከሚገኘው የኤጀንሲው የግዢ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) (ቢሮ ቁጥር-03 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሠነዱን ከመንግስት ንብረት ዋጋ ግምትና ሽያጭ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ (3rd Floor) ቢሮ ቁጥር 02 መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከ2፡30- 6፡30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30-10:30 ሰዓት ብቻ ነው፡፡
  3. የንብረቶቹን ሁኔታ እስከ ሐምሌ 02 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ቀናት ከ2፡30-6:30 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት ድረስ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለፀው ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ በኤጀንሲው ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ሐምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 20% /ሃያ በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ CPO የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ በማዘጋጀትና ከዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 011-1-83-40-636

CPO ለማሰራት፡- የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ /Oromia Public Procurement & Property Disposal Agency/

 

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ

 

Save Tender