Tender Detail

Tender Details


የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር LAMC/BD/04-10/2017 የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በቀድሞ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተረከባቸው ኮንቴነሮች፣ ሶፋዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ ፍሪጅ፣ ጎማዎች፣ የብረትና የጣውላ ሼልፎች፣ ላተራል ፋይል ካቢኔት፣ የባሌስትራ ማሰሪያ፣ መበየጃ ማሽን ቲቪ ስታንድ፣ የፐላስቲክ ወንበርና ጠረፔዛዎች፣ ዋይት ቦርድ፣ ኪችን ካቢኔት፣ ሎከር፣ ካዝ እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ያገለገሉ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር LAMC/BD/04-10/2017 የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በቀድሞ ከመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የተረከባቸው ኮንቴነሮች፣ ሶፋዎች፣ ፈርኒቸሮች፣ ፍሪጅ፣ ጎማዎች፣ የብረትና የጣውላ ሼልፎች፣ ላተራል ፋይል ካቢኔት፣ የባሌስትራ ማሰሪያ፣ መበየጃ ማሽን ቲቪ ስታንድ፣ የፕላስቲክ ወንበርና ጠረፔዛዎች፣ ዋይት ቦርድ፣ ኪችን ካቢኔት፣ ሎከር፣ ካዝ እና ሌሎች ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መመዘኛዎች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡  

  1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ግሎባል በሚገኘው ከንግድ ስራዎች ኮርፖሬሽን ጀርባ ባለው የዕዳ እና የሁበት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ግቢ ውስጥ በሚገኘው በፋይናንስ ኮርፖሬት ሰርቪስ መምሪያ በመምጣት የንብረቶችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡
  2. ንብረቶቹ የሚገኙበት አድራሻ ሳሪስ ከንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ አጠገብ በሚገኘው በሕግ በመፍረስ ላይ ያለ የጥቁር አባይ ኮንስትራክሽን አ.ማ ግቢ ውስጥ ነው።
  3. ተጫራቾች ሰነድ ገዝተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡30 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ልዩ ልዩ ንብረቶች በተራ ቁጥር 2 ላይ በተጠቀሰው ቦታ /አድራሻ/ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡
  4. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 10 በመቶ (10%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 10 ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ5፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም፤
  6. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው ከ7 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፣
  7. የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት ነው።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ንብረቶቹን በ15 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣
  9. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0913-29-26-31/ 0912-13-47-91 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፣
  10. ኮርፖሬሽኑ በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣

 

የዕዳ እና የሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን

አዲስ አበባ

 

 

Save Tender