የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የኤክትሮኒክስ ዕቃዎች ጨረታ ማስታወቂያ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቁሳቁስ ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዚህ ንግድ ዘርፍ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸውን የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀናት 11፡30 ሰዓት ድረስ 200 የማይመለስ በመክፈል ከቢሮው የግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ድረስ የቴክኒካልና የፋይናሻል የመጫረቻ ሰነዶችን ኦርጅናልና አንድ አንድ ኮፒ በተለያዩ ፖስታ በማሸግና ሲፒኦ በቴክኒካል ኦርጅናል ዶክሜንት ውስጥ በመክተትና አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በቢሮ የግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተበሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ታሽጐ 04፡30 ሰዓት ተጫራቾች / ተወካዮቻቸው በተገኙበት በቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት ክፍል ይከፈታል ። ነገር ግን 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመከፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታ ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፤- ዱራሜ አዲሱ ቃለህይወት ቤተከርስቲያን ሉዳ ህንጻ ላይ ይገኛል
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0916863812 ወይም 0911565078
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
