Tender Detail

Tender Details


የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች በየሎቱ በዝርዝር ተቀምጠው ያሉትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Misrak Poly Technic College (የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የሎት ቁጥር

የግዥው ዓይነት

የጨረታ ማስከበሪያ መጠን

ሎት 1

የፅህፈት አላቂ ዕቃዎች

10,000.00

ሎት 2

የፅዳት አላቂ ዕቃዎች

15,000.00

ሎት 3

ደንብ ልብስ አላቂ ዕቃዎች

8,000.00

ሎት 4

የፀጉር ስራ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች

20,000.00

ሎት 5

ICT ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች

80,000.00

ሎት 6

ፈርኒቸር አላቂ ዕቃዎች

40,000.00

ሎት 7

የከተማ ግብርና ቋሚ ዕቃ የወተት ላም እና ዶሮ

30,000.00

ሎት 8

የቢሮ መጋረጃ

5,000.00

ሎት 9

የጥገና ዕቃዎች

9,000.00

ሎት 10

አላቂ የስፖርት እቃዎች

4,000.00

ሎት 11

አላቂ የጥገና እቃዎች

6,000.00

ሎት 12

የህትመት

1,000.00

ሎት 13

የመኪና ጎማ ልብስ እቃዎች

6,000.00

 

  1. ተጫራቾች ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበትን፣ በአቅራቢነት ዝርዝር መመዝገባቸውን እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልጹ ማስረጃዎቻቸውን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ግዥ ዳይሬክቶሬት ሕንፃ 1ኛ ፎቅ ላይ በስራ ሰዓት በመቅረብ እያንዳንዱን ሎት በተናጠል የማይመለስ ብር 150.00 / አንድ መቶ አምሳ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ዋጋ የሚሰጡት ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ብቻ ሲሆን በራሳቸው ሰነድ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርብ ተጫራች ድርጅት ሰነዱ ተቀባይነት አይኖረውም። ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂነቱ ባለቤቱ ይወስዳል።
  4. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ በየሎቱ በተጠየቀው መሠረት በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ብቻ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ምሥራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ስም አዘጋጅተው ማለትም /Addis Ababa City Government TVET Agency Misrak Polytechnic College/ በሚለው ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በመፈረም የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተም በየገፁ በማድረግና የሚወዳደሩበትን ዋጋ በተሸጠላቸው ሰነድ ላይ ብቻ በግልፅ በታሸገ ፖስታ ለየብቻው እንደየሎታቸው ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ በፖስታዎቹ ላይ የሚጫረቱባቸውን የጨረታ ዓይነት በመሙላት የአስተዳደር ሕንፃ አንደኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅታችሁ መሳተፍ የምትፈልጉ ከጥቃቅንና አነስተኛ ጽ/ቤት በኮሌጁ ስም በቅርብ ጊዜ የተፃፈ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች በየንግድ ዘርፋቸው ብቻ መጫረት ይኖርባቸዋል። ከንግድ ዘርፋቸው ውጪ የሚጫረቱ ድርጅቶች ኮሌጁ አያወዳድርም ለሚጫረቱት እያንዳንዱ ነጠላ ዕቃ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል። ሎት 1፣2፤3 ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ ከሦስት ቀን በፊት ጀምሮ ናሙናውን ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ዕለት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በኮሌጁ የሚዘጋጅ ናሙና ሲኖር በግልፅ ቦታ የሚታይ ሲሆን ሌሎች በስፔሲፊክሽናቸው መሰረት የሚወዳደሩ ናቸው።
  8. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታ ቡድን አባላት እና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ በ4፡30 ሰዓት ግዥ ዳይሬክቶሬት የአስተዳደር ሕንፃ ሦስተኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል።
  9. የጨረታ ዋጋ ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ 60 ቀን ይሆናል።
  10. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ፡ 22 ማዞሪያ ከትራፊክ ጽ/ቤት ወደ እንግሊዝ ኤምባሲ በሚወስደው መንገድ ከአስፋልቱ 500 ሜትር ገባ ብሎ ከአዲስ ኮሌጅ ፊት ለፊት ወይም ከእንግሊዝ ኤምባሲ ወደ 22 ማዞሪያ በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ስልክ ቁጥር 0116-18-09-14/0116-18-19-49/0116-18-08-01

 

የምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

 

Save Tender