በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- A-05/2017
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ለ2017 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ አይነት ንብረቶችን /እቃዎችን/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ጨረታ መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች አግባብ ያለው የዘርፉ የታደሰ የዘመኑ የንግድ ፈቃድ፤ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የቫት ሰርተፊኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት /TIN No/፤ ጨረታ እንዲሳተፉ ከገቢዎች የተሰጠ ደብዳቤ እና የወሩ መጨረሻ ለመንግስት ቫት ሪፖርት የተደረገበት ማስረጃ ሁሉም ማስረጃዎች /ንግድ ፈቃዶች/ በተናጠል ኮፒ መደረግ አለባቸው፡፡ የአንዱን ጨረታ ሰነድ ዋጋ የማይመለስ ብር 250.00 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ካምፕ ግዥ ቢሮ ቁጥር፡-02 በመምጣት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ14 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ /BID BOND: CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለበት/GARANTE/::
- የተለያዩ አይነት የፅህፈትና የስልጠና መርጃ እቃዎች ብር 23,561.47
- የተለያዩ አይነት የታካሚ ቀለብ ብር 61,653.28
- የተለያዩ አይነት የፅዳት እቃዎች ብር 108,950.72
- የተለያዩ አይነት የዳቦ ማሽንና ጀነሬተር መለዋወጫ እቃዎች ብር 13,134.00
- የተለያዩ አይነት የተሽከርካሪ አላቂ መለዋወጫ እቃዎች ብር 18,235.55
- የተለያዩ አይነት የግንባታ እቃዎች ብር 97,664.71
ጨረታው ከረቡዕ 10/07/2017 እስከ ማክሰኞ 23/07/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ተሸጦ የሚያልቅበት ቀን ሲሆን ረብዕ 24/07/2017 ዓ.ም በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ3፡45 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በባህር ዳር ከተማ በሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ መኮድ ዋናው ቢሮ አዳራሽ ወስጥ ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- በጨረታው ላይ ያልተገለፁ ዝርዝር ሁኔታዎችን ከፈለጉ ቅፅ 1 ጥር 1998 ዓ.ም በሃገር ውስጥ ለሚፈፀሙ እቃዎችና ተዛማች አገልግሎቶች ግዥ የሚውል መደበኛ የጨረታ ሰነድ ከገንዘብና የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ ላይ ወይም ከመስሪያ ቤቱ በሚገዙት መደበኛ የጨረታ ሰነድ ማየት ይችላሉ፡፡
ስ.ቁ:- 058-3-21-65-82/058-3-21-28-92/09-87-39-48-58
የሰ/ምዕ/ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
