Tender Detail

Tender Details

  • Company አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት
  • Address ክፍለ ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ : ኢትዮጵያ, Phone: 011-213-18-29
  • Website
  • Deadline23 Dec 2024, 9:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Steel, Metals And Aluminium

ድርጅታችን አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች ቤት እድሳት አገልግሎት የሚውል 570 (ኣምስት መቶ ሰባ) ባለ 35 ጌጅ አንደኛ ደረጃ የጣሪያ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት


በድጋሚ  የወጣ  የጨረታ  ማስታወቂያ

 

አዲስ የተቀናጀ የልማት ድርጅት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ወረዳዎች በትምህርት፣ በጤና እና በወጣት ልማት ዘርፎች በርካታ የልማት ሥራዎችን በማከናወን ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ነው።

ድርጅታችን ድጋፍ ለሚያደርግላቸው ቤተሰቦች ቤት እድሳት አገልግሎት የሚውል 570 (ኣምስት መቶ ሰባ) ባለ 35 ጌጅ አንደኛ ደረጃ የጣሪያ ቆርቆሮ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም፤

  • በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 2% በባንከ የክፍያ ትዕዛዝ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ወይም /Tin Number/፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ወይም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ነፃ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች፣
  • ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 07 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ክፍለ ሃገር አውቶቡስ ተራ አዲሱ ሚካኤል አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት በመቅረብ ለዚሁ ሥራ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ /መረጃ/ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ከፍለው በመግዛት የምትሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለጨረታ ማስገቢያ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ አስገብታችሁ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ይጋብዛል።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ8ኛው ቀን ከጧቱ 3:00 ላይ ተዘግቶ ከጧቱ 4:00 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ስምንተኛው ቀን ቅዳሜ ወይም እሁድ ላይ ከዋለ የሚቀጥለው ሰኞ ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ይሆናል።
  • ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ - ስልክ - 011-213-18-29, 011-276-35-39, 09 96 23 09 27

 

አዲስ  የተቀናጀ  የልማት  ድርጅት

Save Tender

አዲስ ማሽንና መለዋወጫ ማምረቻ ኢንዱስትሪ በሀገር አቀፍና በአለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ በብረት ዘርፍ የተሰማሩ አምራች ድርጅቶች፣ በምርት ግብአት ወይም (Dif...

READ MORE
ድርጅታችን ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ የግንባታ ስራዎች አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶችን እና አገልግሎቶችን በቋሚነት የሚያቀርቡ ብቁ አቅራቢዎችን (Suppliers)...

READ MORE
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ለሚከናወነው የግንባታ ሥራ በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ተጫራቾችን በብሔራ...

READ MORE