የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል ፣ EPSONLCD ፕሮጀክተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል
- ሞተር ሳይክል፣
- EPSON LCD ፕሮጀክተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/በመክፈል የጨረታው ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአበሽጌ ወረዳ ፋኢል ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች ከዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፍቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ ወረቀት፤ የምዝገባ ሰርተፍኬት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10000 /ከባንክ በተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ በማያያዝ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕና አስፈላጊውን ማስረጃ ጋር በማያያዝ ኦርጅናል እና ኮፒ ዶክመንት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ተከታታይ የስራ ቀናት 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ወረዳው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011 330 2079 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
ወልቂጤ
