Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 9:30 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Security50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ
  • opening dateተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆን ባልተገኙበት ከቀኑ 4:00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል::
  • Categories Event Organizing And Planning , Audio Visual, Photography And Filming Service And Equipment

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ አስ/በመስቀል አደባባይ ውስጥ ለሚከበረው ከብር በዓል የሚሆን የመድረክ ስቴጅ እና የውጭ አስክሪን ኪራይ ግዢ ጨረታ መሠረት ለማከራየት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መከራየት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅት መካከል አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስ/ ከንቲባ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ መሠረት በሀዋሳ ከተማ አስ/በመስቀል አደባባይ ውስጥ ለሚከበረው ከብር በዓል የሚሆን የመድረክ ስቴጅ እና የውጭ አስክሪን ኪራይ ግዢ ጨረታ መሠረት ለማከራየት በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መከራየት ያስፈለገ በመሆኑ በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅት መካከል አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል::

በዚህ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ ተመሳሳይ ሥራ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው ፤-
  2. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፤
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፤
  4. በጨረታው እንዲሳተፍ የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
  5. .የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ ፤
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይ/ኢ.ኮ/ልማት መምሪያ ቢሮ ( አዲስ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር፤200(ሁለት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ::
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ ኦ (CPO ) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት ::
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ (ፋይናንሻል) በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አሥር) ተከታታይ ቀናት በፋ/ኢ.ኮ/ልማ/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም ) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ታሸጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆን ባልተገኙበት ከቀኑ 4:00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል:: ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል:: የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል ::
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮ/ል/መምሪያ
ሀዋሳ

✨ messages.ai_summary
Hawassa City is seeking licensed firms to rent a stage and outdoor screen for the Meskel holiday celebration at Meskel Square. Bidders must hold a valid business license, VAT registration, tax clearance, and supplier registration.
Save Tender