የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ የጥበቃ አገልግሎት ሰራተኛ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ድርጅቱ ከነማ ፋርማሲ የጽሕፈት መሣሪያዎች የፅዳት እቃዎች፤ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የኮስሞቲክስ እና የወተት ምርቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በስሩ የሚያስተዳድራቸውን ከዚህ በታች በአድራሻቸው የተጠቀሱትን በጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶምኒየም) ላይ የሚገኙትን 3 ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ ለንግድ ቤት አገልግሎት እንዲውል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡፡
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት የተሰጠውን ተግባር እና ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው የድርጅታችንን ሂሳብ አሰራር በአለም-አቀፍ ፋይናሻል ሪፖርቲንግ ስታንዳርድ/ IRFS በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ስለሚፈልግ መስፈርቱን የምታሟሉና ብቁ የሆናቹ ተወዳዳሪዎች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በአዲስ አበባ ከተማና በዙሪያ ለሚገኙ ነዋሪዎች ለሁሉም ክፍለ ከተሞች ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ ለፌደራል ጤና መድህን ተጠቃሚዎች፣ በመንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጥራትና ፈዋሽነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ በ53 መድኃኒት ቤቶች የዱቤ /Credit/ እና ጥሬ ገንዘብ /Cash/ ሽያጭ አገልግሎት እየሰጠ ያለ የመንግስት የልማት ድርጅት ነው። ስለሆነም የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት እንዲያስችለው መድኃኒቶችን በግልፅ ጨረታ በውል ስምምነት ማቅረብ የሚችሉ ብቁ የሆኑ መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።