የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ የጥበቃ አገልግሎት ሰራተኛ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡
Kenema Pharmacy Enterprise (ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት በ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመስሪያ ቤቱ የሚያስፈልጉ የጥበቃ አገልግሎት ሰራተኛ በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በመክፈል ሰነዱን ከግዢ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 306 3ኛ ፎቅ መግዛት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በቼክ ወይንም በባንክ CPO 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና ያለ ቅድመ ሁኔታ (Unconditional) በመስሪያ ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) CPO በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል ይፈራረማል፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነድ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻው በየገፁ ማህተም በማድረግ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ መሆን አለበት ይህ ሳይሆን ሲቀር መ/ቤቱ ቫት እንደተካተተ አድርጎ ይወስዳል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉት ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለተመሳሳይ አገልግሎት ተመሳሳይ ዋጋ ካቀረቡ በዕጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- በጨረታው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ተወዳዳሪዎች በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊ ድርጅት ውል ከተዋዋለ በኋላ ዋጋ መጨመርና መቀነስ የማይቻል መሆኑን ያሳውቃል፡፡
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ
የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎች፤
- በንግድ ዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤
- የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት(የቲን)፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣
- ከግብር ነፃ መሆናቸውን የሚገልፅ ኪሊራንስ፣
- ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን የጥበቃ አገልግሎት ፍቃድ ሰርተፊኬት ያለው፣
- የሰራተኛ ከህሎት ያለውና ኢንሹራንስ ማቅረብ የሚችል እና ቫት ምዝገባ ማስረጃዎች ማቅረብ ይኖርባቹሀል፡፡
አድራሻ፡- ከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
* ከፒያሳ ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ ሰሜን ማዘጋጃ አካባቢ SMSS /ኤስ ኤም ኤስ ኤስ/ ህንፃ
* ስልክ ቁ. 0118-27-87-96
የከነማ ፋርማሲዎች ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Kenema Pharmacy Enterprise seeks bidders for security guard staffing services under an open tender. Bidders must hold a renewed business license, TIN, VAT registration, tax clearance, a Federal Police Commission security service license, and provide staff training and insurance evidence.
