Tender Detail

Tender Details


የአውትሶርስ አገልግሎቶች (አትክልተኛ፣ ጉልበት፣ መኪና ሰርቪስ፣ ጥበቃ) እና ዓመታዊ ግዥዎች (7 ሎት) - የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት ለአንድ አመት የሚቆይ የአውት ሶርስ ስራ ማለትም :- የአትክልተኛ እና የጉልበት ስራ አገልግሎት ፣ የሰራተኞች የመኪና ሰርቪስ ፣ የጥበቃ እና ደህንነት ስራ እና ዓመታዊ ግዥዎች ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ ፣ ሎት 2 ቋሚ ዕቃ ፣ ሎት 3 የደንብ ልብስ ፣ ሎት 4 ኤሌክትሪክ ዕቃ ፣ ሎት 5 የተለያዩ የህትመት ስራ ፣ ሎት 6 የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ፣ ሎት 7 የቧንቧ ዕቃ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ500,000.00 / አምስት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት ፡፡
  3. ተጫራቾች በጨረታ በመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው በየሎቱ ማስገባት እና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. ዝርዝር መግለጫ /እስቴስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላሉ ፡፡ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 / ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመያዝ በአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ ፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲ.ፒ.ኦ በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታሉ ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
  6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4:00 ሰአት ላይ ጨረታ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወዲያው ይታሸጋል ወዲያው 4:10 ላይ ይከፈታል ፡፡
  7. ተማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913675704 /093034113 /0913005480/0913023571 ቁጥር በመደወል መጠየቅ ይቻላል ፡፡
  8. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ 05 / አምስት / ቀን ይቆያል፡፡
  9. የመከፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል ፡፡
  10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያ ተገባር መሆን አለባቸው ፡፡
  11. ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
  12. ግብር የከፈሉበት ክሪላንስ ከገቢዎች ፅ/ቤት አብረው ማስያዝ አለባቸው ፡፡
  13. ውድድሩ የምናወዳድረው በጥቅል ነው ፡፡
  14. ስርዝ ድልዝ ካለው ውድድሩ ሙሉ ለሙሉ ውድቅ ይደረጋል ፡፡
  15. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Ataye Primary Hospital seeks a one-year outsourced services contract (gardening, labor, vehicle service, security) plus annual supplies in 7 lots: stationery, fixed assets, uniforms, electrical items, printing, vehicle spare parts, and plumbing. Bidders need a valid business license, TIN, and VAT registration if annual bid exceeds 500,000 birr.
Save Tender