ኩባንያችን ቡና ኢንሹራንስ አ.ማ ተሽከርካሪዎችን ሞተር ሳይክል ፣ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የቢሮ እቃዎች ፤ ጎማዎች ፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ የተለያዩ የመኪና እቃዎች ፣ የቶነር ካርቲሬጆች ፣ የስልክ ቀፎዎች ፣ ሻተር መጋረጃና የመጋረጃ አክሰሰሪዎች እንዲሁም ምንጣፍ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የጋላፊ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ እቃዎች፣ ስፔርፓርት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ኮስሞቲክስ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ስፔርፓርት እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በሀራጅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ጨ.ቁ 53/2017 ዓ.ም እቃዎቹን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጣቢታ ሪች ኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ድርጅት ንብረት የሆኑትን የተለያዩ ያገለገሉ የቢሮ ጠረጴዛና ወንበሮች፣ የስፌት ማሽኖች፣ የሽመና ማሽን፣ ፍሪጅ፣ ስቶቭ እና የእንጀራ ምጣድ ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
አፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያ በግጭት እና በመገልበጥ አደጋ ጉዳት ደርሶባቸው ለደንበኞች የካሳ ክፍያ ፈጽሞ የተረከባቸውን የተለያዩ አይነት ከባድና ቀላል 7 ተሽከርካሪዎችን እና 14 የመኪና ጋቢናዎች፣ የተለወጡ አሮጌ የተሽከርካሪ ዕቃዎች (ቅሪተ አካሎች) እና 114 የቢራ ሳጥን በቁጥር 1,369 መፅሀፎች፣ 10 ቴሌቪዥኖች እና 2 የተባይ መርጫ ሲሊንደር/ጋን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የኤሌክትሮኒክስ እና ተዛማጅ ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት የሚገኘውን የሠራተኛ መዝናኛ ክበብ በውስጡ የሚገኙ የመስሪያ ቁሳቁሶች (ፍሪጅ፣ ማብሰያ ማሽን፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ የመሳሰሉትን አካቶ) በኪራይ አገልግሎቱን የሚሰጡ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር ለአንድ ዓመት ውል በማስፈረም አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም የመንግስትን ግዥ መስፈርቶች ከሚያሟሉ እና በዘርፉ ከተሰማሩ ህጋዊ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተዉና የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ የመንገድ ግንባታ ማሽነሪዎች (CRAWLER CRANE MACHINE: CEMENT SILO MACHINE) በሀራጅ ጨረታ፣ ተሽከርካሪ በግልጽ ጨረታ እንዲሁም የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን ፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች፣ Galvanized metal coil እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 859/2006 እንደተሻሻለው (1160/2011) መሰረት በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር ያሉ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 10 መሠረት የተወረሱ ንብረቶችን ማለትም ROLLER BEARING፤ SCREW DRIVER SET፤ የህክምና ዕቃዎች፤ VAN PUMP፤ OIL PRESSURE SENSOR ፤TAPERED ROLLER BEARING DOOR FRAME & WATER PURIFIER እና LABORATORY STOOL CHAIR እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የፃግብጂ ወረዳ ገንዘብ ቤት ለወረዳው መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ነገሮችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የተገጠሙ ሊፍቶች፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ የሞተር ሳይክል እና የተሽከርካሪ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ቀፎዎች እና አክሰሰሪው (መገናኛ መሳሪያዎች) እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ለተጫራቾች አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በክልሉ ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ መኪናዎች፣ ያገለገለ ዶዘር፣ ያገለገለ ሎቤድ ተሳቢ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ በተለያዩ ሁኔታ የተቃጠሉ መኪናዎች፣ የመኪና መለዋወጫና ቁርጥራጭ ብረታብረቶች ፣ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ፣ ጄኔሬተሮች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ባህር ዛፎች፣ የጽድ ዛፎች እና የግራር ዛፎችን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የመርካቶ ቁ.2 መ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ያገለገሉ ቋሚ እና አላቂ ንብረቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በመሸጥ ማስወገድ ይፈልጋል።
በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፤ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፤ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፤ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) ባሉበት ሁኔታ በግልፅና በሃራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያ፤ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ እና ሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያየ የቢሮ መገልገያ ማሽኖች ማለትም ፎቶኮፒ ማሽን፣ ፕሪንተሮች፣ ከለር ፕሪንተሮች፣ ኤልሲዲ ፕሮጀክተሮች፣ ላፕቶፕ እና ዴስክቶፕ ኮምፒዩተሮች የመሳሳሉ የኤሌክትሮኒከስ እቃዎችን የጥገና አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለአንድ አመት የሚቆይ የጥገና አገልግሎት መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሄራዊ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ የአረርቲ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ በበጀት ዓመቱ ለኮሌጁ አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ በርካታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የስራ ዘርፎች /የንግድ ዘርፎች የሚገኙ እቃዎችን በግልፅ ጫረታ አወዳድሮ አሸናፊውን በመለየት ለመግዛት ይፈልጋል።
የደ/ ምዕ ኢት/ሕ ክ/ መንግስት በከፋ ዞን ከጨና ወረዳ ፋይ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በየሴክተሩ በተለያዩ ምክንያቶች ተበላሽተው ሳያገለግሉ ቆመው የቆዩ ተሽከርካሪዎችንና የተለያዩ አገልግሎት የማይሰጡ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን እንደየደረጃቸው ግልጽ ጨረታ አውጥቶ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ኩባንያችን ጢስ እሳት ውሃ ስራዎች የአንቲ ቫይረስ፤ የኔትዎርክ ደህንነት መቆጣጠሪያ (Firewall)፣ ዲጅታል ሳይንኤጅ /Floor standing digital signage/፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች፤ የመበየጃ ጄኔሬተሮች እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ፊቲንጎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።