Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያ፤ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ እና ሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


 

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 44/2017

 

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሐዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ የተወረሱ የመገናኛ መሳሪያ፤ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች፣ የቤትና ቢሮ ዕቃዎች፣ ምግብ ነክ፣ የሞተር ሳይክል እና መኪና መለዋወጫ ዕቃዎችና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎችን በግልፅ እና ሐራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ አይገደድም።
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል።
  3. ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ መወዳደር ይችላል።
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O ፣ የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም በሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች ላገለገሉ ሞተር ሳይክሎች ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ለእያንዳንዱ ኮድ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ማሰራት የሚጠበቅበት ሲሆን የአንድ ኮድ ብቻ አሰርቶ በመምጣት አንዱን ሳይሳካ ወደ ሌላው ኮድ መጫረት ተቀባይነት የለውም።
  5. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ወይም በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት መጋዘን ቁጥር 6 (ስድስት) ላይ በተዘጋጀው ቦታ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት መጋዘን ቁጥር-6 (ስድስት) ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ የሚከፈት ሲሆን የግልጽ ጨረታው አልቆ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሐራጅ ጨረታው ይቀጥላል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል /እሁድ/ ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልኩ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው። ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
  7. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
  8. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  10. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  11. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ በሚሰጡት ዋጋ ምክንያት የሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
  12. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።
  13. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።
  14. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96 / 046-212-65-95

 

ጉምሩክ ኮሚሽን የሐዋሳ ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender