Tender Detail

Tender Details


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የተገጠሙ ሊፍቶች፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ላይ የተገጠሙ ሊፍቶች፤ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች

  1. በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት በኮርፖሬሽኑ ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የተለያዩ እቃዎችን ዝርዝር የያዘውን መረጃ ፣ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ዓምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሰጥ ዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ በማሣየት ድምሩን በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 201 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታውቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  3. የዕቃው /ንብረቱ/ ዋጋ በጨረታ ሠነዱ ላይ ዋጋው ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስና ጠቅላላ ድምሩ በሠንጠረዡ መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፤
  4. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመሥርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
  5. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፤
  6. ተጫራቾች ለሚገዙት ንብረት በእያንዳንዱ የስራ ክፍል ስር ለተቀመጡ የቢሮ፣ የግንባታ እና የተለያዩ እቃዎች ሊወገዱ ከቀረቡት ጥቅል የጨረታ ዋጋ ላይ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ሣጥኑ ውስጥ አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርበታል፤
  7. የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛውቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4:30 የተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  8. ሆኖም ተጫራቹ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት እያስተጓጉልም፤ ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፤
  9. የጨረታ መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. በጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፤
  11. ተጫራቾች የጨረታው ውጤቱ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  12. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ 7ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ለኮሮፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤
  13. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመክፈል ዕቃዎቹን በ 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፣ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% /1 /1000/ በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ኮርፖሬሽኑ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል፤
  14. በተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥሮች 011-8-553627 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
  15. ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት፤
  16. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

 

Save Tender