Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama National Regional State Irrigation Development Agency
  • Address Hawassa, Ethiopia, Phone: +251462217860
  • Website
  • Deadline16 Nov 2026, 12:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ለ30 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው::
  • opening dateጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11 ኛው ቀን በ6:00 ሰዓት ይታሸግና በ6:30 ይከፈታል::
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Office And Home Furniture , Electronics Materials

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

Sidama National Regional State Irrigation Development Agency


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 2 ፈርኒቸር
  • ሎት 3 ተሽከርካሪ (ሞተር ሳይክል)
  • ሎት 4 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች
  • ሎት 5 የፅዳት ዕቃዎች

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በውድድር ለመሣተፍ የሚፈልጉ:-

  1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድና TIN ቁጥር ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው::
  2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
  3. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማድረግ በሁለት ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛው ቀን ከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው:
  4. የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ እና የሞተር ሳይክል የጨረታ ሰነድ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ተብሎ ተለይቶ ኦሪጅናልና ኮፒ ማስገባት አለባችሁ::
  5. ተጫራቾች የጠቅላላ ዋጋውን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ለ30 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ አለባቸው::
  6. ከላይ የተገለጹ እቃዎች የጠቅላላ ሽያጭ ከብር 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን ::
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11 ኛው ቀን በ6:00 ሰዓት ይታሸግና በ6:30 ይከፈታል::
  8. በዕለቱ የኤሌክትሮኒክስ እና የተሽከርካሪ የቴክኒካል ሰነድ ብቻ የሚከፈት ይሆናል::
  9. ጨረታው አየር ላይ የሚቀይበት ጊዜ ለ10 ተከታታይ ቀን ቅዳሜና ዕሁድን ጨምሮ ነው::
  10. የሚቀርበው ዋጋ ከላይ የማወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ አንቀጽና ሁኔታ ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት::በተጨማሪም አሸናፊው ተጫራች የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የመንግሥት ግዥ ኤጀንሲ በሀገር ውስጥ ገበያ አነስተኛ ዋጋ ላቀረበ ተጫራች በሚለው መሠረት ተፈፃሚ ይሆናል::
  11. የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በሲ/ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000351753707 ገቢ በማድረግ በኤጀንሲው ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 05 ማግኘት ይቻላል::
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ማሣሰቢያ:-

  • ማንኛውም ከዚህ የመወዳደሪያ ሃሣብ ማቅረቢያ ጋር የተያያዘ /የቀረበ/ ተጨማሪ ሰነድ የተጫራቾችን ፊርማና ማህተም ይፈልጋል::
  • በመወዳደሪያ ሠነድ ላይ ያሉ ሁኔታዎች ከሁሉም በላይ በመወዳደሪያ ሀሣብ ማቅረቢያ የቀረቡትን ሌሎች ተጨማሪ ማረጋገጫዎች ፊርማና ማህተም ካልተደረገባቸው የቀረበው የማወዳደሪያ ሃሣብ ይሰረዛል::
  • አጠቃላይ የዕቃው ዝርዝርና ሲፒኦ ማስያዥያና ማብራሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ ተቀምጧል::
  • ጨረታው ሰነድ ላይ ከጠቀመጠው እስፔክ ውጪ ተጨማሪ እስፔክ በእስክሪፕቶ መጻፍ አይፈቀድም ይህ ሆኖ ቢገኝ ግን ከውድድሩ ውጪ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን::

አድራሻ:- ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ካምፓስ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 221 7860 መጠየቅ ይቻላሉ::

የሲዳማ ብ/ክ/መ/ መስኖ ልማት ኤጀንሲ

✨ messages.ai_summary
Sidama Irrigation Development Agency seeks suppliers of office items in 5 lots: electronics, furniture, motorcycles, office consumables and cleaning items. Bidders need a valid trade licence, TIN, tax payment proof and supplier registration; VAT registration if over 500,000 birr.
Save Tender