የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን የቢሮ ወንበሮችና ጠረጴዛዎች ግዥ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ ብማ/ጨ/03/2019(CB)
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ለዳይሬክቶሬት ቢሮና የመሰብሰቢያ አዳራሽ የሚሆኑ የተለያዩ አይነት ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች፤ ከዘርፉ ከተሰማሩ አምራች/አስመጪ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል::
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | የመዝጊያ ቀንና ሰዓት | የመክፈቻ ቀንና ሰአት | የጨረታ ማስከበሪያ |
| 1 | ለቢሮ ወንበሮች እና ጠረጴዛ | ህዳር 11 ቀን 2019 ከቀኑ 8:00 | ህዳር 11 ቀን 2019 ከቀኑ 8:30 | 50,000/ሀምሳ ሺህ ብር/ |
- ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ https://egp.ppa.gov.et ድረ ገጽ ላይ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡
- የጨረታ ሰነዱን ጥቅምት 26 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000173799946 (EEU-South Addis Ababa Region Customer የኢ.ኤ.አ. የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ከቀድሞ Contribution) በማስገባትና ደረሰኙን ይዞ በመምጣት ጎተራ ሀ ፊት ለፊት ማከቢንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የዋስትና ጊዜው ከሚያበቃበት ቀን በኋላ 28 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ያለውን የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) በኢ.ኤ.አ. የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ብ/ማ/ጨ/0003/2019 (NCB) የሚል ምልክት በማድረግ እና የጨረታ ቁጥሩን በመፃፍ እስከ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በኢ.ኤ.አ የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ከቀድሞ ጎተራ ሀ ፊት ለፊት ማከቢንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ ላይ በመምጣት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም/ ህዳር 11 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ላይ ይከፈታል፤
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጧት ከ2:00-6:00 ከሰዓት 7:00-11:00 እና ቅዳሜ ጧት 2:00- 6:00 ሰዓት ማግኘት ይችላሉ ::
- የፐርቼዚንግ ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-114705377 መደወል ይችላሉ::
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region seeks manufacturers or importers to supply various office chairs and tables for its directorate offices and meeting hall. Bidders need a renewed licence, tax clearance, VAT registration and EGP supplier registration. Open national bid.
