Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500 ብር (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30፣ በተጠቀሱት አድራሻዎች
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

አማራ ባንክ በደብረ ማርቆስ፣ ዳባት፣ ባህርዳር፣ ሸገር፣ ዳንግላ፣ ቡሬና እንጅባራ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር አባ/ሳ፝ፋማ/01/19

አማራ ባንክ አ.ማ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 መሠረት በእዳ ማካካሻነት የወረሳቸውን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

ተ.ቁየተበዳሪው ስምክ/ከተማከተማወረዳቀበሌየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ጨረታው የሚከናወንበት ቦታሊመቻች የሚችል የብድር
1ጥሩነህ ልጃለምደ/ማርቆስደ/ማርቆስ-ቀበሌ 09150 ካ.ሜK/አብ/0025መኖሪያ ቤት2,811,647.91መንቆረር ቅርንጫፍእስከ 70%
2ምንስ ሲሳይአስከተማአስከተማ-ቀበሌ 01150 ካ.ሜይክ/001/1228/011መኖሪያ ቤት1,037,951.89አስከተማ ቅርንጫፍእስከ 70%
3ጥላሁን አደመዳባትዳባት-ቀበሌ 02300ካ.ሜ3635/ታ-302/2011መኖሪያ ቤት4,178,389.48ዳባት ቅርንጫፍእስከ 70%
4አቶ ገብረስላሴ አለሁኝባህርዳርባህርዳር--150 ካ.ሜዳ/ም/ክ/ከ/3504/2014መኖሪያ ቤት G+324,397,135.08ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
5ፋርሚያ አግሪ ግሮ ኃ/የተ/የግ/ማሸገርሸገርአባገዳቀበሌ 01200ካ.ሜSUL/2293/12መኖሪያ ቤት5,362,769.38ዋና መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅእስከ 70%
6ፋርሚያ አግሪ ግሮ ኃ/የተ/የግ/ማሸገርሸገርአባገዳቀበሌ 01200ካ.ሜSUL/2292/12መኖሪያ ቤት5,362,769.38ዋና መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅእስከ 70%
7ፀሃይ አድማስዳንግላዳንግላ-ቀበሌ 01210ካ.ሜ513/0/143መኖሪያ ቤት2,043,821.23ዳንግላ ቅርንጫፍእስከ 50%
8ሀይማኖት ፈቃዴባህርዳርባህርዳር-ቀበሌ 11200ካ.ሜ30/07/05መኖሪያ ቤት G+18,098,805.05ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 50%
9አበበ መልኬቡሬ-ቀበሌ 04200ካ.ሜ8724/2008መኖሪያ ቤት G+1 253ካ.ሜ5,908,629.87ቡሬ ቅርንጫፍእስከ 50%
10ጌትነት መኮንንእንጅባራእንጅባራ--150.09ካ.ሜAM010010603024መኖሪያ ቤት3,287,146.17እንጅባራ ቅርንጫፍእስከ 50%
11ጌትነት መኮንንእንጅባራእንጅባራ--249.97ካ.ሜAM010010311005መኖሪያ ቤት5,005,112.73እንጅባራ ቅርንጫፍእስከ 50%
12ግርማ እርቀየሱስባህርዳርባህርዳር--1,000ካ.ሜአዒቲ/9389/2014መኖሪያ ቤት23,303,728.19ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 50%

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሂሳብ ቁጥር ETB1756800010001 የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለገሀር በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅ ሳፓላይቼንና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ፣ ባህርዳር ዲስትሪክት፣ ዳባት ቅርንጫፍ፣ ዳንግላ ቅርንጫፍ፣ ቡሬ ቅርንጫፍ፣ አስከተማ ቅርንጫፍ፣ እንጅባራ ቅርንጫፍ፣ መንቆረር ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በአቅራቢያቸው ከሚገኙ የአማራ ባንክ ቅርንጫፎች በባንኩ ስም ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በማሰራት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይችላሉ። ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲ.ፒ.ኦ አይመለስለትም፣ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል::
  4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፣ ግብር፣ ከስም ማዛወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል::
  5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፣የመንጃ ፍቃድ፣ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል::
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካውትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል::
  8. ጨረታው ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተ.ቁ1 በተጠቀሱት አድራሻዎች በተመሳሳይ ጊዜ እና ሰዓት ይካሄዳል።
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ለተጫራቹ ከ50% እስከ 70% ብድር ሊያመቻች ይችላል ::
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
  12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል::
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ፡- 011-558-2660 ወይም በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

አማራ ባንክ አ.ማ

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is auctioning 12 foreclosed residential houses in Debre Markos, Ask Ketema, Dabat, Bahir Dar, Sheger, Dangila, Bure and Injibara. The bank may finance 50% to 70% of the price for eligible winners. Public auction.
Save Tender