ስኬት ባንክ በአዲስ አበባና ሸገር የሚገኙ ቤቶች፣ ተሽከርካሪና የአክሲዮን ድርሻ የሐራጅ ሽያጭ
Siket Bank S.C (ስኬት ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ስኬት ባንክ አ.ማ (የቀድሞ አዲስ ብድርና ቁጠባ ተቋም አ.ማ) ብድር ሲሰጥ በመያዣነት የያዛቸውን ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና እንደተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
1. ለጨረታ የቀረቡ መኖሪያ ቤቶች
| ተ/ቁ | የተበዳሪው ስም | የዋሱ ስም | የቤቱ ዓይነት | ብድሩ የወጣበት ቅርጫፍ | ከተማ/ክ/ከተማ | ክ/ከተማ/ ወረዳ | የቤቱ ካርታ ቁጥር | የቦታ ስፋት በካ.ሜ | መነሻ ዋጋ (በብር) | ቀን | ሰዓት (ጠዋት) | ለሐራጅ የቀረበው |
| 1 | ኢቲፌ መርጋ | አማሩ አሼቱ | መኖሪያ | አለምገና | አዋሽ መልካ | አዋሽ መልካ | BMA/0031/09 | 200 | 362,208 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
| 2 | ቤቦኒሸ ትሬዲንግ ሃ/የተ/የግ/ማህበር | ደሳለኝ ወርቁ | መኖሪያ | ልደታ | ሸገር | ገላን ጉዳ | OR005022906018 | 213.68 | 8,156,673 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
| 3 | አፀደ እስራኤል እና ጓደ.ሀ.ሽ.ማ | ምትኩ ገብሬ | መኖሪያ | ጉርድ ሾላ | አ.አ/ለሚ ኩራ | 06 | AA0000611019517370764 | 109.25 | 5,317,744 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
| 4 | ኤን መብሬ ሃ/የተ/የግ/ማ | ሽታዬ ጋሻዉ | የንግድ ቤት | ጎፋ | አ.አ/ን/ስ/ላ | 08 | NL130141454109013347 | 109 | 3,728,792 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
| 5 | ነቢል ሙንታሃ እና ጓ/ሀ/ሽ/ማ | መዲና ሙሃመድ | መኖሪያ | አየር ጤና | ሸገር/ፉሪ | ገዳ ፉጂ | L/S/27024/2002 | 140 | 4,345,076 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
| 6 | ብሩክ ሞላ | ሞላ ጀንበር | መኖሪያ | ቦሌ ቡልቡላ | አ.አ/ቦሌ | 12 | BL1231537581504042 | 150 | 12,040,887 | 08/04/2019 | 3:00-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
2. ለሐራጅ የቀረበ ተሽከርካሪ
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የዋስ ስም | ቅርንጫፍ | የሠሌዳ ቁጥር | የመኪናው ዓይነት | መነሻ ዋጋ | ቀን | ሰዓት(ጠዋት) | ለሐራጅ የቀረበው |
| 1 | በለዉ ዘለቀ | በተበዳሪ ስም | ከዛንቺስ ሂልተን | 03-39578 ኦ.ሮ | 2L-ዶልፊን | 1,000,000 | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | ለመጀመሪያ ጊዜ |
3.ለሐራጅ የቀረበ የአክሲዮን ድርሻ
| ተ.ቁ | የተበዳሪ ስም | የሠር. ቁጥር | አውጪ ተቋም | የአክሲዮኑ ብዛት | መነሻ ዋጋ (በብር) | ቅርንጫፍ | ቀን | ሰዓት | ለሐራጅ የቀረበው |
| 1 | ዕጹብ ረዘነ | 016449 | እናት ባንክ | 476 | 476,000 | ጀሞ | 07/04/2019 | 3:00-6:00 | በድጋሚ |
ማሳሰቢያ
- ማንኛውም ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሉ የቤቶቹን/የተሽከርካሪዎን/የአክሲዮን ድርሻውን ሐራጅ መነሻ ዋጋ ¼ኛውን በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲፒኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ በማስያዝ መጫረት ይችላል ::
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ ጨረታውን ማሸነፉቸውን በማስታወቂያ ሰሌዳ ከተለጠፈበት ቀን አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ያለበት ሲሆን ካልከፈሉ ለሐራጅ መነሻ ያስያዘው ገንዘብ ተመላሽ አይደረግለትም::
- ጨረታ የወጣው ተሽከርካሪ ከመስከረም 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 07 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ብር 11,218/አስራ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አስራ ስምንት ብር/ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብር አለበት።
- ጨረታ ከወጣው ተሽከርካሪ ከመንግሥት የሚፈለግ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)፣ የቦሎ ክፍያ፣ የስም ማዛወሪያ እና ሌሎች ወጪዎችን የጨረታው አሸናፊ ይሸፍናል::
- ተራ ቁጥር 4 ላይ የተጠቀሰው ንግድ ቤት ከመንግስት የሚፈለግ የካፒታል ትርፍ ግብር(Capital gain tax) ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::
- ተራ ቁጥር 1,2,3,4,5 ላይ የሚገኙት የቤቶች ጨረታ የሚከናወነው ፒያሳ ቸርችል ጎዳና በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ሲሆን ፤ ተራ ቁጥር 6 ላይ የተጠቀሰው መኖሪያ ቤት ጨረታው የሚካሄደው መኖሪያ ቤቱ በሚገኙበት አድራሻ ቅጥር ጊቢ ውስጥ ይሆናል::
- የተሽከርካሪው እና የአክሲዮን ድርሻው ጨረታ የሚካሄደው ፒያሳ ቸርችል ጎዳና በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ነው::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከጨረታው መከፈቻ ሰላሳ ደቂቃ ቀደም ብሎ ይጀመራል::
- ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስት አካል ደብዳቤ ይፅፋል ::
- ቤቶቹን እና ተሽከርካሪውን ለማየት ሚፈልጉ ተጫራቾች ጨረታው ከሚከናወንበት 10(አስር) ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት ህግ ክፍል በመመዝገብ ባንኩ በሚያመቻቸው ፕሮግራም ቤቶችን/ተሽከርካሪውን መጎብኘት ይቻላል፤በተጨማሪም ብድሩ በተሰጠበት ቅርጫፍ ፅ/ቤት በስራ ቀናት በመሄድ ቅርንጫፉ በሚሰጠው ፕሮግራም መሰረት መኖሪ ቤቶቹን መጎብኘት ይቻላል::
- ስም ማዘዋወሪያ፣የሊዝ ክፍያ እና ሌሎች ውዝፍ ክፍያዎች እንዲሁም ገዥ እንዲከፈላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስና ግብሮችን ገዥው/አሸናፊው ይከፍላል::
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ጨረታውን ካካሄደው የባንኩ የሕግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይሆናል::
- በጨረታዉ ቀን የንብረቱ ባለቤት ወይም ህጋዊ ወኪሉ በመገኘት ጨረታውን መከታተል ይችላሉ፤ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል::
- ባንኩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 8342 ወይም 011-1-279028 በመደወል ወይም በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሕግ አገልግሎት በግንባር ቀርቦ መጠየቅ ይቻላል::
ስኬት ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Siket Bank is auctioning collateral: five residential houses and one commercial building in Addis Ababa and Sheger City, a 2L-Dolphin vehicle and 476 shares in Enat Bank. Bidders deposit a quarter of the starting price. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
