Tender Detail

Tender Details

  • Company ቡና ባንክ አ.ማ
  • Address , Phone: 0111580863
  • Website
  • Deadline10 Dec 2026, 9:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4ኛ (CPO)
  • opening dateታኅሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም፣ በየቅርንጫፉና ዋና መሥሪያ ቤት
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

ቡና ባንክ በአዳማ፣ አዲስ አበባ፣ ጋምቤላ፣ ይርጋለምና ጢጢቻ የሚገኙ የመኖሪያ ቤቶች የሐራጅ ሽያጭ

ቡና ባንክ አ.ማ


የሐራጅ ማስታወቂያ

ቁጥር፤ ቡባ/ሕአዳ/ሐራጅ/05/2019

ቡና ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁ. 97/1990 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ተ.ቁ.የተበዳሪ ስምየንብረት አስያዥ ስምአበዳሪ ቅርንጫፍለጨረታ የቀረበው ንብረትከተማ/ክ/ከተማ/ቀበሌ ወረዳ/ የቤት ቁጥርየካርታ ቁጥርየቦታ ስፋትየጨረታ መነሻ ዋጋ በብርጨረታው የሚከናወንበት ቀንሰዓትጨረታው የወጣው
1አቶ ከበበው አየለ ተሰፋዬተበዳሪአዳማቅይጥ ይዞታ መኖሪያ ቤትኦሮሚያ ብ/ክ/መንግሥት፣ አዳማ ከተማ (ቀበሌ 04 አዳማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ.)OR001143505012200.75 ካ/ሜ5,873,005.07ታኅሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም4:00-5:00ለሁለተኛ ጊዜ
ቅይጥ ይዞታ መኖሪያ ቤትኦሮሚያ ብ/ክ/መንግሥት፣ አዳማ ከተማ (ቀበሌ 04 አዳማ ዩኒቨርሲቲ አካባቢ.)OR001143505013199.63 ካ/ሜ7,643,677.37ታኅሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም5:00-6:00ለሁለተኛ ጊዜ
2ጊ.ስታር ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበርአቶ ዮሴፍ ደስታ ሰብስቤዓባይመኖሪያአዲስ አበባ ከተማ፣ ቦሌ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12 (ቦሌ ቡልቡላ አካባቢ.)BO-LTP-BO12000498-014836500 ካ.ሜ42,000,000.00ታኅሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም4:00-5:00ለመጀመሪያ ጊዜ
3አቶ ቸርነት ሲጋሮ ወዳጆተበዳሪጋምቤላመኖሪያ ቤትበጋምቤላ ሕ/ብ/ክ/መ፣ ጋምቤላ ከተማ፣ ቀበሌ 04፣823/89417 ካ.ሜ.2,921,618.61ታኅሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም3:00-4:00ለሦስተኛ ጊዜ
4አቶ ሙላቱ ሽጉጤ ጀሮተበዳሪይርጋለምየመኖሪያ ቤትበሲዳማ ብ/ክ/መንግስት፣ ይርጋለም ከተማ፣ ዳሌ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ አካባቢ የሚገኝ፤SD006050508017373.747 ካ/ሜ3,120,055.82ታህሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም3:00-4:00ለሁለተኛ ጊዜ
5አቶ አሸናፊ ቱማቶ ቱንሲሳተበዳሪአየር ጤና 05የመኖሪያ ቤትሲዳማ ጢጢቻ ከተማ ቀበሌ 01 (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጢጢቻ ቅርንጫፍ አካባቢ.)RN/195/14300 ካ.ሜ1,300,382.42ታህሳስ 1 ቀን 2019 ዓ.ም3:00-4:00ለሦስተኛ ጊዜ

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በቡና ባንክ አ.ማ ስም በማሠራት ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
  2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ተጠቃሎ መከፈል አለበት:: ካልተከፈለ የተያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃሉ:: ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ በዕለቱ ይመለስላቸዋል::
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ብቻ ናቸው:: ተበዳሪ እና ወኪሎቻቸው ባይገኙም ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
  4. የተጫራቾች ምዝገባ ከእያንዳንዱ የንብረት ሐራጅ መዝጊያ ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል:: በሐራጁ የመጨረሻ ሰላሳ ደቂቃዎች የተጫራች ምዝገባ አይካሄድም::
  5. የሐራጁ አሸናፊ /ገዢ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎችን፣ ግብር በዋጋው ላይ የሚታሰብ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛወሪያ ክፍያ ጋር የተገናኙና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው /አሸናፊው/ ይከፍላል::
  6. በሐራጁ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ለማየት ከአበዳሪ ቅርንጫፉ ጋር በመነጋገር ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል::
  7. ተጫራቹ የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው አሸናፊነቱን የሚገልፅ ደብዳቤ በጽሑፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
  8. ጨረታው በተራ ቁጥር 1 ላይ ለተገለጸው ንብረት በቡና ባንክ አ.ማ አዳማ ቅርንጫፍ፣ በተራ ቁጥር 3 ለተገለጸው ንብረት በቡና ባንክ አ.ማ ጋምቤላ ቅርንጫፍ፣ በተራ ቁጥር 4 እና 5 ለተገለጹት ንብረቶች በቡና ባንክ አ.ማ ይርጋለም ቅርንጫፍ የሚካሄድ ሲሆን፣ በተራ ቁጥር 2 ለተገለጸው ንብረት በቡና ባንክ አ.ማ ዋናው መሥሪያ ቤት ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ወደ ቦሌ ሲሄዱ ሩዋንዳ መታጠፊያ ሳይደርሱ በሚገኘው የባንኩ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚካሄድ ይሆናል::
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ፡- ሕግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስ.ቁ 011-1-58-08-63/ 011-1-26-36-09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

ቡና ባንክ

✨ messages.ai_summary
Bunna Bank is auctioning six foreclosed residential properties in Adama, Addis Ababa (Bole), Gambela, Yirgalem and Titicha. Bidders deposit a quarter of the starting price by CPO. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender