ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopia Commodity Exchange (ECX)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: ኢም.ገ/ግልጽ ጨረታ ቁ001/2019
- ኢትዮጵያ ምርት ገበያ ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
- ያገለገሉ የአልሙኒየም ፓርቲሽን እና መስታወት እቃዎች ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም. ድረስ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ 1 6ኛ ፎቅ ዘወትር በስራ ስአት ከሰኞ እስከ አርብ 2:30-6:30 ከሰአት 7:30-10:00፤ እንዲሁም ህዳር 16 ቀን 2019 እስከ ጠዋቱ 5:00 ድረስ ብቻ በአካል በመገኘት ማስገባት ይቻላል።
- ስለ አገሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሠነድ ሜክሲኮ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ 1 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 514 የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በቴሌ ብር በመክፈል ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ህዳር 16 2019 ከጠዋቱ 5:00 ድረስ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የእቃ ዓይነት በጥቅል የጨረታ የመነሻ ዋጋቸውን 10% (አስር ፐርሰንት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ (Ethiopia Commodity Exchange) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ህዳር 16 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 5:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 5:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ምርት ገበያ አልሳም ጨለለቅ ህንፃ 1 6ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾቹ በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉለውም፣
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ: ሁሉም እቃዎች የሚገኙበት ቦታ በኢትዮጲያ ምርት ገበያ በዋና መስሪያ ቤት አልሳም ጨለለቅ ህንፃ ሜክሲኮ የሚገኙ ናቸው።
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ
✨ messages.ai_summary
Ethiopia Commodity Exchange (ECX) sells used aluminium partitions and glass through a tender. The items are at its head office in Alsam Chelelek Building, Mexico, Addis Ababa. Open to all interested bidders.
