የአፍሪካ ቪሌጅ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን እና በተቋሙ የሐራጅ ሽያጭ ፖሊሲ መሰረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች የተመለከተውን ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
Africa Village Microfinance S.C (የአፍሪካ ቪሌጅ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.)
የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ 1020
የአፍሪካ ቪሌጅ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን እና በተቋሙ የሐራጅ ሽያጭ ፖሊሲ መሰረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውን ከታች የተመለከተውን ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
| ተ.ቁ. | የመያዣው ባለቤት | የመኪናው አይነት | የመያዣው ግምት /የጨረታ መነሻ ዋጋ/ | ቦታ | ቀን | ሰዓት |
| 1 | አቶ የቢጋሸት ገብሬ | የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ጃ.ን- 450፣ አአ-03-B75552 | 964,982.50 | ዋና መ/ቤት | 19/3/2019 | ከጠዋቱ 3-5 |
ተጫራቾች መኪናውን በአ/አበባ ከተማ፣ቂርቆስ ክ/ከ ልዩ ቦታው ጎተራ፣መስቀል ፍላወር ያሬድ ቤ/ክርስቲያን ምዕራብ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች ጨረታው በሚካሄድበት ቦታ ቀንና ሰዓት በአካል ተገኝቶ ወይም በሕጋዊ ወኪሉ በኩል መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሲመጡ የታደሠ የቀበሌ/ፋይዳ መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- በውክልና የሚጫረት ሰው በሚመለከተው የመንግሥት አካል የጸደቀ ውክልና ዋናውንና ኮፒውን ይዞ መቅረብ አለበት።
- ማኅበርን ወይም በሕግ ሰውነት የተሰጠውን አካል ወክሎ መጫረት የሚፈልግ ሰው ከማኅበሩ ወይም ከላከው አካል ውክልና ይዞ መቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ለጨረታ ሲቀርቡ የሚጫረቱበትን ንብረት የጨረታ ዋጋ 1/4ተኛውን በጥሬ ገንዘብ (ካሽ) ወይም በአፍሪካ ቪሌጅ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ስም በተዘጋጀ እና በባንክ የተረጋገጠ/ሲፒኦ/ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታውን ያሸነፈ ሰው ያሸነፈበትን ዋጋ አጠቃሎ በ15 ቀን መክፈል ያለበት ሲሆን በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙትን ገንዘብ (ሲፒኦ) ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- የጨረታ አሸናፊው ቀሪውን ገንዘብ በ15 ቀን ውስጥ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ተወርሶ በመያዣው ላይ ሌላ ጨረታ ይወጣበታል።
- በጨረታ አሸናፊ የገዛ በሽያጭ ገንዘብ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ከንብረቱ ጋር የተያያዙ ለመንግሥት የሚከፈሉ ክፍያዎች እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጪዎች ይከፍላል።
- አክስዮን ማኅበሩ በብድር ፖሊሲው መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ብድር ሊያመቻች ይችላል።
- አክሲዮን ማኅበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሊሰርዝ ይችላል።
ለበለጠ መረጃ-በስልክ ቁጥር 0984084446 / 0114398248
አፍሪካ ቪሌጅ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ.
✨ messages.ai_summary
Africa Village Microfinance S.C. sells by open auction a repossessed electric automobile held as loan collateral, as is. The vehicle can be viewed at its head office in Gotera, Kirkos Sub-City, Addis Ababa, where the auction is held. Open to individuals and organisations.
