ወላይታ ልማት ማህበር በወላይታ ዞን ከተሞች የሚገኙ የንግድና የመኖሪያ ቤቶች ሽያጭ (አራተኛ ዙር)
Wolaitta Development Association (የወላይታ ልማት ማህበር)
አራተኛ ዙር የወጣ የቤት ሽያጭ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ልማት ማህበር የቤት ሽያጭ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር ወልማ/004/2026
ወላይታ ልማት ማህበር ማህበሩን ለማጠናከር በመካሄድ ላይ በሚገኘው ልዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም በወላይታ ዞን (ወላይታ ሶዶ፣ጠበላ፣ ጉኑኖ ዲምቱ፣ ሃሳሴ፣ ጎጮ፣ ጋቼኖ፣ ጃጊ፣ ገሱባ ከተማ እና ቡጌ) ከተሞች የሚገኙ ለንግድና መኖሪያ አገልግሎቶች ሊውሉ የሚችሉ የመጀመሪያ ፣ሁለተኛ፣ ሶስተኛ እና አራተኛ ጊዜ ለጨረታ የሚወጡ ቤቶችን ባሉበት ሁኔታ በአራተኛ ዙር የግልጽ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- በጨረታ የሚሳተፉ ግለሰቦች ከሆኑ ህጋዊ መታወቂያ፣ ድርጅቶች ከሆኑ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ህጋዊ የመታወቂያ ካርድ ፣ህጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የሥራ ቀናት 15ኛው ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓትና ቀን ወላይታ ሶዶ ከሚገኘው ወላይታ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል እና የወላይታ ልማት ማህበር ቤቶቹ ለጨረታ በወጡባቸው ከተሞችና ወረዳ አስተዳደሮች በሚገኙ ትርንጫፍ ጽ/ቤቶች የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ [...] 10% ለቤቱ ሽያጭ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋ መሰረት በማናቸውም ንግድ ባንኮች የተመሠከረለት በወላይታ ልማት ማህበር ስም የተሠራውን ሲ.ፒ.ኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሠነድ ጋር አያይዘው በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን አንስቶ ለሚቆጠር 15 የሥራ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆይና በ15ኛው ቀን በዕለቱ ከሰዓት 9:00 ሰዓት ታሽጎ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9:15 ሰዓት ወላይታ ሶዶ በሚገኘው የማህበሩ ዋና ጽ/ቤት ግዥ፣ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ክፍል በይፋ ይከፈታል።
- 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በካላንደር ዝግ ከሆነ ለሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፍና ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ቤት ኮድ በመምረጥ የመጫረቻ ሰነዳቸውንና ዋጋ ማቅረቢያውን ሳይዘለል፣ ሳይታለፍ ስርዝ ድልዝ ሳይገኝበት በሙሉ አጠናቅቆ በመሙላት ኮፒና ኦርጂናል በተለያየ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውስጥ ማስገባት አለበት።
- የጨረታው ሃደት የሚከናወነው ተጫራቹ መግዛት ለሚፈልገው ቤት ያቀረበውን ጠቅላላ ዋጋና ሰነዶችን መሠረት በማድረግ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች የጨረታው አሸናፊ መሆኑ በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ5 የሥራ ቀኖች ውስጥ በመቅረብ ውል መግባት የሚኖርበት ሲሆን፤ ይህን ካልፈጸመ ጨረታውን በፈቃዱ እንደሰረዘ ተቆጥሮ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ ለድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቹ በጨረታው ማሸነፉን በማስታወቂያ ከተገለጸበት ቀን አንስቶ በ10 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያሸነፈበትን ቤት ዋጋ በተገባው የውል ስምምነት መሰረት ገንዘቡን በማህበሩ አካውንት ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- በጨረታ ያሸነፉትን ቤቶች ውል ለማጽደቅ፣ ስም ለማዛወርና ማናቸውንም ተያያዥ ወጪዎች ገዥው ይሸፍናል።
- ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቤቶቹ በሚገኙበት ከተማ ማህበሩ በሚያመቻቸው ሰዓት ተገኝተው መመልከት ይችላሉ።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
- የጨረታ ሠነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልጽ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ በመንተራስ ዋጋ ማቅረብ አይፈቀድም።
- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ተጨራቾች ተጨማሪ መረጃ ወይም ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል መቅረብ ወይም ስልክ ቁጥር 0910541363/0913255729 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ወላይታ ልማት ማህበር
✨ messages.ai_summary
Wolaitta Development Association is selling, in a fourth round, commercial and residential houses as-is in Wolaita Sodo, Tebela, Gununo Dimtu, Hasase, Gocho, Gacheno, Jagi, Gesuba and Bugie towns. Bidders deposit 10% of the starting price by CPO.
