ሂጅራ ባንክ በሰመራ ከተማ የሚገኝ የመኖሪያ ቤት የሐራጅ ሽያጭ
Hijra Bank S.C
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ሂጅራ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/90 (እንደተሻሻለው) በተሰጠው ስልጣን መሰረት በዋስትና የያዘውን ንብረት ባለበት በሐራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | ለጨረታ የቀረበው መያዣ ንብረት | ፋይናንስ ያደረገው ቅርንጫፍ | ከተማ | ክ/ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የካርታ ቁጥር | የቦታው ስፋት በካርታ | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚከፈትበት ቀን | ሰዓት | ጨረታው የወጣው |
| 1 | ሙኩታር ሰይድ መሀመድ | ሙኩታር ሰይድ መሀመድ | የመኖሪያ ቤት | ሎጊያ- ሱልጣን ቃሊም ቅርንጫፍ | ዓፋር ክልል | ሰመራ ከተማ | - | 01 | ሠ/ሎ/ከ/አ 821/12 | 600 ካ.ሜ² | 4,188,706.29 | ታህሳስ 06 ቀን, 2019 ዓ.ም | ከቀኑ 8:00 ሰዓት | ለመጀመሪያ ጊዜ |
- ተጫራቾች ከጨረታ ቀን በፊት ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ቀርበው ማየት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ ሀያ አምስት በመቶ(25%) የጨረታ ማስከበሪያ ቦንድ በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.አ አሰርተው ከጨረታው ቀን በፊት ማስያዝ ወይንም ጨረታ በሚከሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ጨረታው ሰንጠረዥ ላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ባለዕዳዎቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በዓፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሂጅራ ባንክ ሎጊያ ሱልጣን ቃሊም ቅርንጫፍ ይካሄዳል::
- በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው የጨረታ ቀን ባለዕዳዎቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል::
- በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ጨረታውን ካካሄደው የባንክ ክፍል ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል::
- ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል::
- ንብረቱ በአሸናፊው ተጫራች ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
- ለተጨማሪ መረጃ ዋና መ/ቤት የህግ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአካል ወይንም በስልክ +251115584508/0913080624 መጠየቅ ይቻላል::
- ጨረታው ከመካሄዱ በፊትም ሆነ ከተካሄደ በኋላ ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም ዕዳው ከተከፈለ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ጨረታውን ያሸነፈው ተጫራች ለመንግስት የሚከፈለውን የስም ማዛወሪያ፣አስፈላጊውን ግብር እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ይከፍላል::
- የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ የሚከፈለውን ክፍያ ለመክፈል ንብረቱ በሚገኝበት የወረዳ ወይም የከተማ አስተዳደር በማቅረብ የሊዝ ውል መዋዋል አለበት::
ሂጅራ ባንክ አ.ማ
✨ messages.ai_summary
Hijra Bank is auctioning a foreclosed residential house on a 600 square metre plot in Semera town, Afar Region. Bidders deposit 25% of the starting price by CPO. Public auction.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
