ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ለተለያዩ የመ/ቤቱ ስራ የሚውሉ መኪናዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ለተለያዩ የመ/ቤቱ ስራ የሚውሉ መኪናዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል::
በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሰነዱን በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚችሉት ከህዳር 04ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት አዳማ ከተማ አሮጌው ፖስታ ማህበር ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሰርቪስ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) ብር በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ::
- ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት በሚመጡበት ወቅት የዘመኑን ግብር የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ዋናውን እና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል ::
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ውስጥ እንደተገለፀው የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ ከታወቀ ባንክ ተረጋግጦ በሚቀርብ ዋስትና (CPO) 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዶቻቸው ላይ የጨረታውን ስም፤ የተጫራቹን ሙሉ ስም እና አድራሻ በትክክል መጻፍ አለባቸው::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኅዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል::
- ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲመልሱ ስርዝ ድልዝ ያለዉ ሰነድ ተቀባይነት የለውም::
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲ.ፒ.ኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 022-111-0994 / 022-112-3550 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን
✨ messages.ai_summary
Ethio Telecom South East Region (Adama) seeks vehicle owners to rent vehicles for various office operations. Bid documents are sold at its Adama office. Open bid.
