Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 5% (CPO)
  • opening dateህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Sales, Disposals And Foreclosure

አማራ ባንክ በባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ብርሃን፣ ቡሬ እና እንጅባራ የሚገኙ የፋብሪካ መጋዘኖች እና የንግድ ህንጻ የሐራጅ ሽያጭ

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ ቁጥር አባ/ሳቼፋማ/02/19

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

አማራ ባንክ አ.ማ የሰጠው ብድር ባለመከፈሉ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና በተሻሻለው 216/92 መሠረት [...] ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁየተበዳሪው ስምክ/ከተማከተማወረዳቀበሌየቦታው ስፋትየባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥርየንብረቱ ዓይነት/ አገልግሎትየጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ጨረታው የሚከናወንበት ቦታባንኩ ሊያመቻች የሚችለው የብድር መጠን
1አቶ ሚካኤል በውዱጠባሴደ/ብርሃን-ቀበሌ075,000ካ.ሜደብኢፓ/0382/2011የፋብሪካ መጋዘን24,891,914.22ደ/ብርሃን ዲስትሪክትእስከ 100%
2[...] ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማጣናባህርዳር-9,000ካ.ሜባህኢፓ/0188/11የፋብሪካ መጋዘን135,113,138.21ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 100%
3አቶ ግርማ እርቀየሱስአፄቴዎድሮስባህርዳር--2,500 ካ.ሜባህኢፓ/0241/11የፋብሪካ መጋዘን38,989,862.42ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
4ወ/ሮ ሀይማኖት ፈቃዱመሸንቲባህርዳር--8,000ካ.ሜባህኢፓ/0306/12የፋብሪካ መጋዘን43,509,198.74ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
5አቶ ወርቁ መሀባውመሸንቲባህርዳር--10,000ካ.ሜባህኢፓ0288/2012የፋብሪካ መጋዘን37,690,967.12ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
6አቶ ወርቁ መሀባውአዘዞጎንደር-ቀበሌ203,000ካ.ሜ10792/2008የፋብሪካ መጋዘን22,597,616.89ጎንደር ዲስትሪክትእስከ 70%
7አማዋ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማጠባሴደ/ብርሃን-ቀበሌ097,500.57ካ.ሜደብኢፓ/0382/2011የፋብሪካ መጋዘን11,555,852.95ደ/ብርሃን ዲስትሪክትእስከ 70%
8አቶ ዮሴፍ ነጋቡሬቡሬ--6,300ካ.ሜBIAIP/006/2012የፋብሪካ መጋዘን20,006,475.78ቡሬ ቅርንጫፍእስከ 70%
9ዘጌ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማጣናባህርዳር-ቀበሌ1610,000ካ.ሜባህኢፓ0188/11የፋብሪካ መጋዘን80,727,619.07ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
10ዘጌ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማጣናባህርዳር-ቀበሌ1610,000ካ.ሜ33730/09የፋብሪካ መጋዘን101,763,561.54ባህርዳር ዲስትሪክትእስከ 70%
11አቶ ታደሰ ቢጋለእንጅባራእንጅባራ-ቀበሌ04180.38ካ.ሜ6017/06ያላለቀ የንግድ ህንጻ G+520,446,249.22እንጅባራ ቅርንጫፍእስከ 50%

ማሳሰቢያ

  1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሂሳብ ቁጥር ETB175680001000I የማይመለስ 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ለገሃር በሚገኘው በዋናው መስሪያ ቤት 20ኛ ፎቅ ሳፕላይቼንና ፋሲሊቲ ማኔጅመንት መምሪያ፣ ባህርዳር ዲስትሪክት፣ ጎንደር ዲስትሪክት፣ደ/ብርሃን ዲስትሪክት፣ ቡሬ ቅርንጫፍ፣ እንጅባራ ቅርንጫፍ ዕ/ቤቶች ዘወትር በስራ ሰዓት ከጥቅምት 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ መመዝገብ ይችላሉ::
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 5% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በኢትዮጲያው ከሚገኙ የአማራ ባንክ ቅርንጫፎች በባንኩ ስም ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በማሰራት ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ማስገባት ይችላሉ። ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
  3. የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል። ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል::
  4. የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ከስም ማዛዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/ አሸናፊው/ ይከፍላል::
  5. ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤የመንጃ ፍቃድ፤ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል::
  6. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
  7. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል::
  8. ጨረታው ህዳር 10 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተ.ቁ1 በተጠቀሱት አድራሻዎች [...]
  9. ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም። ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል።
  10. በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ለተጫራቹ ከ50% እስከ 100% ብድር ሊያመቻች ይችላል ::
  11. የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
  12. በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል::
  13. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  14. ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 011-558-2660 ወይም በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::

አማራ ባንክ አ.ማ.

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is auctioning 11 foreclosed properties, mainly factory warehouses in Bahir Dar, Gondar, Debre Birhan and Bure, plus an unfinished G+5 commercial building in Injibara. Bank loans may be arranged for winners. Public auction.
Save Tender