Tender Detail

Tender Details

  • Company Boru Meda General Hospital (ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል)
  • Address ደቡብ ወሎ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 033-2-41-50-05
  • Website
  • Deadline19 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityሎት 1 የጽህፈት መሳሪያ 20,000፤ ሎት 2 የፅዳት እቃዎች 20,000፤ ሎት 3 የጥገና እቃ 20,000፤ ሎት 4 ህትመትና ቅፃቅፅ 10,000፤ ሎት 5 መድሃኒት የህክምና መሳሪያ እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት 25,000 — ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ (በቼክ ማስያዝ አይቻልም)
  • opening date4:30 ይከፈታል።
  • Categories Printing And Publishing , Cleaning And Janitorial Equipment , Pharmaceutical Products , Medical Equipment And Supplies , Laboratory Equipment And Chemicals , Stationery Materials

የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

Boru Meda General Hospital (ቦሩ ሜዳ ጠቅላላ ሆስፒታል)


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የቀረበውን ዝርዝር በግልፅ ጨረታ ዘዴ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች በቀረበው ሎት ዝርዝር መሰረት:-

ተ.ቁሎትየጨረታው ዓይነትየጨረታ ማስከበሪያየውድድሩ አይነትምርመራ
1.ሎት 1የጽህፈት መሳሪያ20,000በሎትለ1 አመት
2.ሎት 2የፅዳት እቃዎች20,000በሎትለ1 አመት
3.ሎት 3የጥገና እቃ20,000በነጠላለ1 አመት
4.ሎት 4ህትመትና ቅፃቅፅ10,000በሎትለ1 አመት
5.ሎት 5መድሃኒት የህክምና መሳሪያ እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት25,000በነጠላ
  1. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ለሁሉም ሎት የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ (የስራ ፍቃድ) ያላቸው። የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ግዥው ከ500,000 አምስት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነ እቃ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎቱ 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰአት በሆስፒታል ግቢ በመቅረብ ከዛሬ ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር ቀናት) ቀን ውስጥ በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ዋናና በስም በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ወይም ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል። በተጠቀሰው ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል። መጫረቻ ሰነድ ላይ ሲሞሉ ለሁሉም ሎት ቫትን ወይም TOT ጨምሮ መሆን ይኖርበታል። ለሁሉም ሎቶች የውለታ ማስከበሪያ በመመሪያው መሰረት ውል ይወስዳሉ።
  5. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ ገቢ በማድረግ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ከጨረታው ሰነዱ ጋር አብሮ በቀረበው የጨረታ መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ንብረቶችን መረካከቢያ ቦታ ሆስፒታል ግቢ ይሆናል። ሆ/ሉ ቫት ሰብሳቢ መሆኑን እናሳውቃለን። የጨረታ ማስከበሪያ በቼክ ማስያዝ አይቻልም።
  7. የጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ 45 ቀን
  8. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች በሚከፈትበት ቀን ቢኖሩም ባይኖሩም ከመከፈት የሚያስተጓጉል ነገር አይኖርም። የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን የሚሆን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር:- 033 241 50 05 /ደውለው ይጠይቁን።

የቦሩ ሜዳ ጠ/ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Boru Meda General Hospital buys by open tender in five lots: stationery, cleaning items, maintenance items, printing, and medicines, medical equipment and lab reagents. Bidders need a renewed trade licence for each lot, paid tax, TIN and VAT for purchases over 500,000.
Save Tender