Tender Detail

Tender Details

  • Company ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
  • Address መካኒሳ አቦ ቤተክርስቲያን አጠገብ ኩዊንስ ህንጻ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 14 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 11 23 84 29
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ጠቅላላ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  • opening dateጨረታው ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4:00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል::
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Used Items

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) በቁጥር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር


የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር -Disposal MIG -MCE 0003/2019

የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባል የሆነው ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር ለሥራ አገልግሎት ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) በቁጥር 10,000 /አስር ሺህ/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

በዚሁ መሠረት:-

1. ተጫራቾች አዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 08 ከመካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ከኩዊንስ ሱፐርማርኬት ቀጥሎ ባለው የኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅታችን ዋና መስሪያ ቤት በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ የድርጅቱ ፋይናንስ ቢሮ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ::

2. በጨረታው ለመሣተፍ ግለሰብ ወይም ድርጅት መሆን ይችላል:: በጨረታ የሚሣተፈው ድርጅት ከሆነ በኢትዮጵያ ውስጥ የተቋቋመ መስሪያ ቤት በበጀት ዓመቱ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰነድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች በጨረታው ለሚሳተፉባቸው ጠቅላላ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ/CPO/ በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በጥንቃቄ አንብበው የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዳቸውን እንዲያቀርቡ ይመከራሉ::

5. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ካለው ውድድሩ ከመፈፀሙ በፊት የጨረታ ተሣታፊዎች ባሉበት ሣይነበብ ውድቅ ይደረጋል::

6. ጨረታው በሚካሄድበት አዳራሽ ውስጥ መገኘት የሚችሉት ሲፒኦ ያስመዘገቡ ተጫራቾች ብቻ ናቸው::

7. ተጫራቾች ቃሊቲ አዲሱ ተርሚናል ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጥቅምት 29 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 07 ቀን 2019 ዓ.ም ባሉት ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) በአካል በመገኘት ማየት ይችላሉ::

6. ተጫራቾች የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ መሰረት የሚገዙበትን የአንድ በርሜል ዋጋ ከቫት በፊት እና ቫትን ጨምሮ በመጥቀስ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰአት ጥቅምት 29 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ረፋድ 4:00 ድረስ ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ አድራሻ የንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያና ሲፒኦ በሰም በታሸገ ፖስታ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ:: ጨረታው ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት ከረፋዱ 4:00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ጠዋት ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል::

7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት/ አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ6 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነበትን የሬንጅ ባዶ በርሜሎች(Bitumen Barrel) ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ንብረቱን ማንሳት ሲኖርበት ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO የማይመለስ ይሆናል::

8. አሸናፊ ድርጅት /ግለሰብ/ የሬንጅ ባዶ በርሜሎች (Bitumen Barrel) የመጫን፣ የማጓጓዝ እና ሌሎች ተዛማጅ ወጪዎችን በራሱ ይሸፍናል::

9. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጫራቾች እንዲመለስ ይደረጋል::

10. ሻጭ ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው::

አድራሻ:-ልደታ ክፍለ ከተማ መካኒሣ አቦ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ ኢትዮ አግሪሴፍት ቅጥር ግቢ ውስጥ

ማሳሰቢያ:-

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር:- +251911900960 /+2510919487762 ይጠቀሙ::

ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል::

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

✨ messages.ai_summary
MIDROC Construction Ethiopia, a MIDROC Investment Group member, sells 10,000 used empty bitumen barrels through an open tender. Barrels can be inspected at the Kality new terminal. Open to individuals and companies; companies need a renewed trade licence, TIN, VAT and tax clearance.
Save Tender