Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
  • Address , Phone:
  • Website
  • Deadline20 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ የሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ የብር /30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/ CPO በወልቂጤ ፖ.ሊ ቴክኒክ ስም አሰርቶ ማቅረብ ይኖርበታል::
  • opening dateበዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል::
  • Categories Stationery Materials , Educational And Training Equipment And Machinery

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ን/ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ፕሮግራሞች ስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ቋሚና አላቂ እቃዎችን ለመግዛት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርት የሚያሟሉ አቅራቢ ን/ድርጅቶች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: በዚህም መሰረት በጨረታው ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች በሙሉ

  1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የዘመኑ ግብር መከፈላቸው የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት አቅርቦት ጋር ተዛማጅነት ያለው ንግድ ፈቃድ በእቃ አቅራቢ ዝርዝር የተመዘገቡበት ሰርተፍኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ / V.A.T/ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው እንዲሁም የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ /TIN / መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወልቂጤ ፖ.ሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ሂሳብ ቁጥር 1000026941737 ገቢ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ የግ/ን/አስ/ደ/ስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 04 መቅረብ መግዛት ይችላሉ::
  4. ማንኛውም ተጫራች ለውድድሩ የሚያቀርቡት የጨረታ ዶክመንት ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በማንኛውም ህጋዊ ባንክ የተረጋገጠ የብር /30,000/ ሰላሳ ሺህ ብር/ CPO በወልቂጤ ፖ.ሊ ቴክኒክ ስም አሰርቶ ማቅረብ ይኖርበታል::
  5. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ7 ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውሉን ማስከበሪያ አሸናፊ ከሆነባቸው እቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  6. የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች ለውድድር የሚያቀርቡት ዋጋ ከኮሌጁ ከሚገዙት የጨረታ ዶክመንት ላይ በመሙላት ዋናው /ኦርጅናል/ እና ኮፒው ለየብቻ በስም በታሸገ ፖስታ አድርገው በፖስታው ላይ የኮሌጁ ስም እና ጨረታ ቁጥር በመፃፍ የንግድ ድርጅቱ ስም እና ማህተም በማድረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 15 ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ
  7. ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ ለውድድሩ ዋጋ ሞልቶ የሚያቀርበው ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ላይ ብቻ ሲሆን በእያንዳንዱ የጨረታ ዶክመንት ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ማድረግ አለበት::
  8. ተጫራቾች ከጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ /CPO / ጨምሮ ማንኛውም መረጃዎች ለውድድር ከሚያቀርቡት ኦርጅናል የጨረታ ዶክመንት ጋር ተያይዞ መቅረብ አለበት::
  9. ጨረታው ማስታወቂያው ከወጣበት በተከታታይ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጐ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ የግዥ ኬዝ ቲም ክፍል ይከፈታል:: ጨረታ የሚከፈትበት እለት በአል ወይንም የእረፍት ቀን ከሆን በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰአት የሚታሽግና የሚከፈት ይሆናል::
  10. አሸናፊው ውል ተፈራርሞ ካጠናቀቀበት ጊዜ አንስቶ በ15 ቀናት ውስጥ ያሸነፈባቸውን እቃዎች ሙሉ በሙሉ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ ኮሌጁ ድረስ አቅርቦ ማስረከብ ይኖርባቸዋል::
  11. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው::
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ሁኔታ ቫትን /የተጨማሪ እሴት ታክስ / ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል:: ይህ ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ተብሎ ይወሰዳል::
  13. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

ለበለጠ መረጃ:- በስ.ቁጥር 011 365 8463 ይደውሉ

የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Wolkite Polytechnic College seeks suppliers of fixed and consumable items for its training programs, delivered to the college. Bidders need a renewed trade licence, tax payment proof, supplier registration, VAT and TIN certificates.
Save Tender