Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ.ዩኒየን /ሳጃ/
  • Address ሳጃ ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 10 29 27 80
  • Website
  • Deadline18 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300.00 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 20,000.00 (CPO)
  • opening dateበ16ኛው ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት
  • Categories Transportation Service And Cargo , Freight Transport

የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ. ዩኒየን /ሳጃ/ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ.ዩኒየን /ሳጃ/


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ መለያ ቁጥር የምተ 01/2019

ተ.ቁሎትየተፈለገው አገ/ትየጨረታ ማስከበሪያ/CPO/
1አንድደረቅ ጭነት አገ/ት20,000.00
  1. የዩኒየኑን ህጋዊ ደንብ የሚያከብርና ከማንኛውም ሰነ ምግባር ችግር የፀዳ፤
  2. የተለያዩ የዘር ወቅት ሁኔታ፣ የጣቢያዎቹ ኮታ፣ የመጋዘን ጥበትና የመሳሰሉትን ችግሮች ታሳቢ በማድረግ የዞኑ ግብዓት ኮሚቴ የሚያስቀምጣቸውን ወቅታዊ አቅጣጫዎች ተቀብሎ ለመስተናገድ ፍቃደኛ የሆነና የመተባበር ባህርይ ያለው፤
  3. የአገ/ት ክፍያን በተመለከተ የጊዜ ገደብ እየሰጠ ተረጋግቶ ከሸያጭ ገቢ መቀበል የሚችል፤
  4. በዘርፉ የታደሰ የሥራ ፍቃድ፣የንግድ ምዝገባና የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ የተ.ኢ.ታ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር / TIN/ ዋናና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው::
  5. ተጫራቾች የጨረታና የውል ማስከበሪያ የ20,000.00 ብር /CPO/ አሰርቶ ማቅረብ አለባቸው::
  6. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 300.00 ብር በመክፈል ወስደው በተዘጋጀው ቅጽ ላይ በግልጽ በአማርኛ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት መጠየቂያውን ሙሉ በሙሉ በመሙላት በፖስታ በሚገባ አሽጎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ መክተት አለባቸው:: የፈለጉትን ቦታ ብቻ መርጠው መሙላት አይቻልም::
  7. በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
  8. ዩኒየኑ ከማንኛውም ጨረታ አሸናፊ ጋር የራሱን አይሱዙ መኪና አሰማርቶ የማሠራት መብት አለው::
  9. የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ታዛቢዎች ባሉበት ይከፈታል:: ሆኖም የተጫራቾች ያለመገኘት ጨረታ መክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን አያስተጓጉልም::
  10. የጨረታ አሸናፊ ወዲያው የሚገለጽ ቢሆንም ጨረታው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህ/ሥራ ኮሚሽን ፀድቆ እስኪቀርብ በትዕግስት መጠበቅ አለበት::
  11. በክልሉ ፀድቆ ሲቀርብ የጨረታ አሸናፊ ቀርቦ ውል ገብቶ ማጓጓዝ እንዲጀምር ጥሪ ይደረጋል::
  12. ጨረታውን ያላሸነፉት ጨረታው ከፀደቀ ከ28 ቀናት በኋላ ሰነዶቻቸውንና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
  13. በጨረታው ላይ ቅሬታ ለማቅረብ የሚፈልግ ቅሬታውን ጨረታው በተከፈተ እስከ 3 ቀናት ውስጥ ብቻ ለየም ዞን ሕ/ሥራ ጽ/ቤትና ለዩኒየን ጽ/ቤት በጽሑፍ በማመልከቻ ማቅረብ ይችላል::
  14. ከ 3 ቀናት በኋላ ከየትኛውም አቅጣጫ የሚቀርብ የቅሬታ አቀራረብ ተቀባይነት አይኖረውም፤
  15. ዩኒየኑ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ወይም አስገዳጅ ሁኔታዎች ከገጠሙት ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  16. መመዝገቢያ ጊዜ:- ይህ አዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ባሉት የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ይሆናል::
  17. መመዝገቢያ ቦታ:- በሳጃ ከተማ ከአ/አበባ ጂማ በሚሄደው አስፋልት ላይ 240 ኪ/ሜትር በየም ዞን ሕ/ሥራ ል/ጽ/ቤት ግብዓትና ግብይት ዳይሬክቶሬት እና በፎሩ ለሚመዘገቡት በዩኒየኑ ጽ/ቤት ሂሳብ ክፍል ዘወትር ሥራ ሰዓት በአካል በመቅረብ ይሆናል፡
  18. ዩኒየኑ ጨረታውን የሚሰርዝበት አጋጣሚ ከተፈጠረ ለተጫራቾች ገንዘባቸውን ወድያው ይመልሳል:: ለበለጠ መረጃ 0910292780/0942356924/0913197219 ይደውሉ::

ቴሌግራም 0952198603 ኢሜይል yemtebaberunion @.com

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየም ዞን የየም ተባበር ገበሬዎች ሕ/ሥራ ኃ.የተ. ዩኒየን/ሳጃ/

✨ messages.ai_summary
Yem Tebaber Farmers Cooperative Union (Saja, Yem Zone, Central Ethiopia) seeks licensed dry cargo truck owners to transport agricultural inputs. Bidders need a renewed licence, trade registration, VAT and TIN, and must accept the zone input committee's allocation directions. Open bid.
Save Tender