Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address የሀዲያ ዞን ፣ኢትዮጲያ, Phone: 046-555-2337
  • Website
  • Deadline24 Nov 2026, 1:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 300 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 85,000 (CPO ወይም ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበ22ኛው ቀን 8:00
  • Categories Building Construction

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የበሌሳ፣ ምርሱጦ እና ሁማሮ ጤና ጣቢያዎች የፋርማሲ ብሎኮች ቀሪ ስራዎች ግንባታ ጨረታ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዲያ ዞን ጤና መምሪያ የበሌሳ ፣ ምርሱጦ እና ሁማሮ ጤና ጣቢያ የፋርማሲ ብሎኮች ቀሪ ስራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት፡-

  1. ደረጃቸው BC-7/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከዞን ፋይ/ኢ/ል/መምሪያ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 21ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በመያዝ መግዛት ይችላል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በአሠሪው መ/ቤት ስም 85,000 /ሰማንያ አምስት ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንስ ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ እና የቴክኒካ ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጅናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴክኒካ ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና ሁለቱንም የቴክኒካል እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ እናት ፖስታ በማድረግ የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 22ኛው ተከታታይ ቀናት 7፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች) ተሞልቶ፣ ተፈርሞና ታሽጎ መመለስ አለበት፤ የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) መጠይቆች (ባዶ ቦታዎች) ሳይሞሉ ማህተም ብቻ አድርጎ መመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
  4. ጨረታው በ22ኛው ቀን በ8፡00 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥ ፋይ/ን/አስተዳደር አዳራሽ ይከፈታል፤ 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።

መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡- የተሻሻለው የክልሉ መንግስት ግዥ አዋጅ ተፈጻሚ ይሆናል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 46 555[...] ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ሆሳዕና

✨ messages.ai_summary
Hadiya Zone Finance Department seeks contractors to complete the remaining works on pharmacy blocks at Belesa, Mirsuto and Humaro health centers for the Zone Health Department. Open to BC-7/GC-7 or higher contractors registered with the Ministry of Urban Development and Construction.
Save Tender