የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጌሜዶ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ግንባታ ጨረታ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የዞኑ ጤና መምሪያ ለሚያስገነባው ለጌሜዶ ጤና ጣቢያ ቀሪ ስራዎች ግንባታ የሥራ ተቋራጮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት፣
- ደረጃቸው BC-7/GC-7 እና ከዚያ በላይ የሆነ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ምዝገባ ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል የጨረታ ሰነዱን ከሀዲያ ዞን ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማስታወቂያው ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ 25ኛው ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ባለፈቃዱ ወይም ሕጋዊ ተወካዩ አንድ ኮፒ የሰነድ ማስረጃ በማስያዝ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም 100,000 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee letter/ ከፋይናንሻል ሰነድ ጋር በፖስታ በሰም አሽገውና ማህተም በማድረግ ፈርመው ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች አስፈላጊውን ዕቃና ሠራተኛ አቅርበው ሥራውን የሚሠሩበትን የፋይናንሻል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ ሰነዶችን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም አራቱንም ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና የፕሮጀክቱን ስም ጠቅሶ የቴክኒካል ፕሮፖዛል አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒ ሰነዶች እንዲሁም ኦርጂናል ቴክኒካል ሀሳብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ አራቱንም የቴክኒካል ሰነዶች በሌላ አንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎ የቴክኒካ እንዲሁም የፋይናንሻል ፖስታዎች በአንድ ማጠቃለያ ፖስታ በሰም አሽጎና ሁለቱንም ስም ጠቀሶ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ሣጥን ውስጥ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 26ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በእጅ የተሞሉ ኮፒ ሰነዶች ማቅረብ ከጨረታው ውድድር ውጭ ያደርጋል። የአገልግሎት ዋጋው በሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ቦታ በአሃዝና በፊደል መሞላት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል የቴክኒካል ሃሣብ የያዘ ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) በየመጠይቁ (ባዶ ቦታዎች ተሞልቶ ተፈርሞና መሃተም ተደርጎ ታሽጎ መመለስ አለበት። የቴክኒካል ሃሣብ የያዘውን ሰነድ (Bidder Certification of Compliance) አለመመለስ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
- ጨረታው በ26ኛው ቀን በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሀዲያ ዞን ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፤ 26ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡-
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የመንግስት የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ተፈጻሚ ይሆናል።
- ማንኛውም ተጫራች ከወቅቱ ገበያ ዋጋ በታች ያቀረበ እንደሆነ ለሰሪው መ/ቤት ውል ለመግባት አይገደድም።
- ማንኛውም ተጫራች በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ (EGP) የተመዘገበ መሆን አለበት።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር [ቁጥሩ በማስታወቂያው ላይ አልተገለጸም]
የሀዲያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ሆሳዕና
✨ messages.ai_summary
Hadiya Zone Finance Department seeks contractors to complete the remaining construction works of Gemedo Health Center for the Zone Health Department. Open to BC-7/GC-7 or higher contractors registered with the Ministry of Urban Development and Construction and on EGP.
