ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎች ላይ ለሚፈለገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Berhan Bank S.C (ብርሃን ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ብርሃን ባንክ አ.ማ ከባለእዳዎች ላይ ለሚፈለገው ገንዘብ በዋስትና የያዛቸውን እና ከዚህ በታች የተመለከቱትን ንብረቶች በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 216/92 ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች በመገንዘብ ማክበር ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን የ1/4 (አንድ አራተኛ) (ሲፒኦ) በብርሃን ባንክ አ.ማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማሰራት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ::
- የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን እንዳሸነፈ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ አለበት:: በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ይመለስላቸዋል::
- የመኖሪያ ቤቶቹ እና የቡና ኢንዱስትሪው ጨረታ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ይከናወናል::
- የጨረታ አሸናፊው በሚገዛው ንብረት ላይ የሚፈለግ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈል ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያዎች እና የሊዝ ክፍያዎች ይመለከተዋል::
- መያዣ ሰጪዎች ሐራጁ በሚከናወንበት ቦታ ቀንና ሰዓት መገኘት ይችላሉ:: ባይገኙ ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል::
- በባንኩ ብድር መመሪያ መሰረት እና በተሰጠው ጊዜ ውስጥ የሚፈለገውን ለሚያሟላ ተጫራች ባንኩ በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል::
- ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት ይቻላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው::
የመኖሪያ ቤት እና የቡና ኢንዱስትሪ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የመያዣ ሰጭው ስም | መኖሪያ/ የንግድ ቤት የሚገኝበት አድራሻ | የቦታው ስፋት በካሬ ሜትር | የንብረቱ አገልግሎት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ካርታ ቁጥር | የጨረታ መነሻ ዋጋ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት፤ |
| 1. | ሲንጤ አብዲልሃቅ | ሲንጤ አብዲልሃቅ | አዳማ ከተማ ቦኩ ሸነን ቀበሌ | 105.2 ካ.ሜ | መኖሪያ ቤት | OR001176105008 | 2,700,000.00 | ህዳር 21 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-5:30 |
| 2. | ሀሴና ፈይሳ | ሀሴና ፈይሳ | ሰንዳፋ ከተማ 01 ቀበሌ የፓርሴል መለያ ቁጥር HC-81 | 200 ካ.ሜ | መኖሪያ ቤት | 210/955/98 | 1,350,000.00 | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-5:30 |
| 3. | አመቤት ጌታቸው | አመቤት ጌታቸው | ሰንዳፋ በኬ ከተማ 02 ቀበሌ | 200 ካ.ሜ | መኖሪያ ቤት | 470/1740/99 | 2,500,000.00 | ህዳር 22 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00-9:30 |
| 4. | ሃና ታደሰ | ሃና ታደሰ | ቢሾፍቱ ከተማ 05 ቀበሌ ቁጥር R-33(ኮንዶሚኒየም) | 50.06 ካ.ሜ | መኖሪያ ቤት | ME/M1/B6/4TH/R33/2 | 1,600,000.00 | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-5:30 |
| 5. | ቤንች ማጂ ጨካ ቡና አምራቾች ኃ/የተ/የህ/ስራ ዩኒየን | የቤ/ማ ጨካ ቡና አምራቾች ኃ/የተ/ህ/ ስራ ዩኒየን | ሰሜን ቤንች ወረዳ ቤንች ሼኮ ከተማ ደቦር ደማዜ ቀበሌ | 33000 ካ.ሜ | የቡና ኢንዱስትሪ | 03 | 4,300,000.00 | ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00-5:30 |
በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 መሰረት የተሰጠ ማስጠንቀቂያ፤
ለአቶ እንየው ተሾመ ታደሰ እና ወ/ሮ ሰላሳይ አፈራው ሀ/ስላሴ
ስማችሁ ከላይ የተጠቀሰው የብርሃን ባንክ አ.ማ ተበዳሪ በገቡት የብድር እና/ወይም መያዣ ውል መሰረት መክፈል የሚጠበቅባችሁን ክፍያ ባለመክፈላችሁ ምክንያት ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ባስመዘገባችሁት አድራሻ ልትገኙ ያልቻላችሁ እና ማስጠንቀቂያውን ለመውሰድ ፍቃደኛ ባለመሆናችሁ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት አልተቻለም:: ስለሆነም ይህ ማስጠንቀቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ያለባችሁን ቀሪ ዕዳ አጠናቃችሁ እንድትከፍሉ እየጠየቅን፣ በተሰጠው ጊዜ ውስጥ መክፈል ካልቻላችሁ ባንኩ በአዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት እርምጃ የሚወስድ መሆኑን እናሳውቃለን::
ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 011-6506900 እና 011-6506276 በመደወል መጠየቅ ይቻላል::
✨ messages.ai_summary
Berhan Bank is auctioning, as is, five properties held as loan collateral: residential houses in Adama, Sendafa (two) and a Bishoftu condominium, and a 33,000 sq m coffee industry in Sheko town, Bench area.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
