የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት የቧንቧ መገጣጠሚያ፣ ተሽከርካሪ ጋሪ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ አልባሳትና ጫማ ግዥ
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የእቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2019
የደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከህጋዊ ነጋዴዎች ለመግዛት ይፈልጋል። ለጨረታ የቀረቡ እቃዎችም፡
- ቧንቧ መገጣጠሚያ
- ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ
- የጽህፈት መሳርያ
- ብትን ጨርቅ
- የተሰፋ ልብሶች
- የወንድ እና ሴት ጫማ
- ልብስ ስፌት
በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች በማሟላት በጨረታ መወዳደር ይችላል።
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የተመዘገቡ፣ በተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ ከሆኑ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- ለጨረታ ዋስትና ከሚቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ፣ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት / በጥሬ ገንዘብ/ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ድርጅቱ በሚያቀርበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ሰዓት ደ/ማ/ ከተማ ውሃ አገልግሎት አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን የተለያየ ፖስታ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ደ/ማ/ከ/ው/አገ/አዲሱ ቢሮ ገቢ ግዥ ፋይ/ንብ አስ/የስ ሂደት ቢሮ ቁጥር 11 ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሰም አለመታሸጉ ከጨረታ ውጭ አያስደርግም።
- ሰርፌስ ፓምፕ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያችሁን እና ቴክኒካል ሰነዳችሁን ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማስገባት ይኖርባኋል።
- በ15ኛው ቀን የጨረታ ሳጥን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ይታሸጋል። ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን እሁድ ወይም የካላንደር ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 3፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በማጓጓዝ ደ/ማ/ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስቶር ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የማጓጓዣውንም ሆነ የሠራተኛ ጉልበት ዋጋ ድርጅቱ አይሸፍንም።
- ተጫራቾች የሚፈፅሟቸው ሌሎች ግዴታዎች በጨረታ ሰነዱ ላይ እና ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው የተጫራቾች የግዥ መመሪያ ላይ በተቀመጠው አግባብ ይሆናል።
- ድርጅቱ በጨረታው የተሻለ ዘዴ /መንገድ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- የቧንቧና መገጣጠሚያ እቃዎች፣ ሸሚዝ እና ብትን ድርጅቱ በሚያቀርበው ናሙና መሰረት ማቅረብ ያለባችሁ በመሆኑ ዋጋ ከመሙላታችሁ በፊት ውሃ አገልግሎት ድርጅት ድረስ በመምጣት የእቃ ናሙናውን እንድታዩ እያሳሰብን፤ የእቃውን ፎቶ ግራፍ አይታችሁ ዋጋ የምትሞሉ ፎቶ የእቃን አይነት እንጅ የእቃ ጥራትን ስለማያሳይ በአካል መጣችሁ ናሙናውን እንድታዩ እናስታውቃለን።
- ርክክብ የሚፈፀመው ከተቀመጠው ናሙና ጋር አንድ አይነት መሆኑ ሲረጋገጥ ብቻ ነው።
አድራሻ፡- ደ/ማ/ከ/የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁ 0587716840፣ 0587711058፣ 0587711520
ደብረ ማርቆስ ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Debre Markos City Water Supply and Sewerage Service Enterprise seeks suppliers of pipe fittings, three-wheel carts, stationery, fabric, ready-made clothes, men's and women's shoes and tailoring, matching its samples. Open to licensed, registered traders.
