ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማስያዣነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
Global Bank Ethiopia S.C
የቤቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: 04/2026/27
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ለሰጠው የብድር ማስያዣነት በአዋጅ ቁጥር 97/1990 መሠረት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
| ተ.ቁ | የንብረቱ ዓይነትና የሚሰጠው አገልግሎት | ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ - ከተማ | ክ/ከተማ | ቀበሌ/ ወረዳ | የቦታው ስፋት በካ.ሜትር | የካርታ ቁጥር | አስያዡ ቅርንጫፍ | የጨረታ መነሻ ዋጋ |
| 1 | የታሸገ ውሃ ማቀነባበሪያ እና መጋዘን | ሸገር | ሰበታ | አዋስ | 6000 | WLBEN/7679 | ሆሳዕና | 28,000,000.00 |
| 2 | መኖሪያ ቤት | ጎንደር | ሳንጃ | 01 | 340 | 00 831 | ጎንደር | 1,400,000.00 |
| 3 | መኖሪያ ቤት B+G+4 ህንጻ | አዲስ አበባ | ቂርቆስ | ወረዳ 01 | 133.35ካ.ሜ x 4 114.01ካ.ሜ x 1 | 000040101642 AA 000040101642 AA 000040101642 000040101642 AA AA 000040101642 AA | ስታዲየም | 65,000,000.00 |
| 4 | መጋዘን | ሸገር | ገላን | ገላን ቀበሌ | 6300 | BMG/K/L/I/TA/2014 | ዉሉስፎር | 95,000,000.00 |
| 5 | የንግድ ሕንጻ (G+4) | ሻሸመኔ | ቡልቻና | 05 | 889 | 163 | አዋሳ | 60,000,000.00 |
የጨረታው ደንቦች፡-
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ስታዲየም ቅ/ፍ የሚመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና ግሎባል ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ ላይ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ /ፎርም/ መውሰድ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋውን 20% (ሃያ በመቶ) በገንዘብ ክፍያ ማዘዣ /CPO/ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ስም በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ /ናሽናል ቢዝነስ ሴንተር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ/ በአካል በመቅረብ እስከ ሕዳር 9 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ማንኛውም ተጫራች ሌሎች ተጫራቾች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያካተተ መሆን አለበት:: ይህንንም በግልጽ ማሳየት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራች ድርጅት ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት፣ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርበታል::
- አሸናፊ የሚሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በ30 /ሠላሳ / ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ከባንኩ ጋር የሽያጭ ውል መግባት አለበት::ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብም ካሸነፈበት ገንዘብ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ማሸነፉ ከተገለጸለት በኋላ እስከ 30ኛው ቀን ድረስ አስፈላጊውን የሽያጭ ውል የማይፈጽም ከሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 /ስልሳ/ ቀናት ይሆናል::
- በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የገንዘብ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ውሳኔ እንዳገኘ ተመላሽ ይደረጋል::
- ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዛወር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል የትብብር ደብዳቤ ይጽፋል::
- ለመንግስት ማንኛውም ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ ንብረት በማስተላለፍ ሂደት የሚኖር ክፍያ እና ሌሎች ማንኛውንም ክፍያዎች ገዢው ይከፍላል::
- ጨረታው ሕዳር 9 ቀን 2019 ከጠዋቱ 4:00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከጠዋቱ 4:15 ሰዓት ላይ በግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት 7ኛ ወለል ላይ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል::
- መረጃ እና የንብረቶቹን አጠቃላይ ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ዋናው መ/ቤት ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ በስልክ ቁጥር 0115 58 12 04 ወይም 0115 31 80 97 በመደወል እና ቀጠሮ በማስያዝ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋት 2:00 – 6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7:00 — 11:00 ሰዓት ቅዳሜ ጠዋት ከ2:00 — 6:00 ሰዓት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሕዳር 8 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ መጎብኘት ይችላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ሊጋራ ስኬታችን!
✨ messages.ai_summary
Global Bank Ethiopia sells five foreclosed properties: a water bottling plant and warehouse and a warehouse in Sheger, a house in Gondar, a B+G+4 residential building in Addis Ababa and a G+4 commercial building in Shashemene. Company bidders need trade licence, VAT, TIN and tax clearance.
