Tender Detail

Tender Details

  • Company በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል
  • Address አዲስ አበባ ሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ /ገነት ሆቴል/ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0939500000
  • Website
  • Deadline09 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና
  • opening dateአሰረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  • Categories Land, House, Building And Warehouse Rent

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ለሕፃናት መጫወቻ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ የገነት ሆቴል


የልጆች መጫዎቻ ስፍራ እና የስፖርት ማዝወተሪያ ቦታ ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በሆስፒታሊቲ ዘርፍ ከሚተዳደሩ የልማት ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ገነት ሆቴል አስተዳደር በሆቴሉ ግቢ ውስጥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች ለሕፃናት መጫወቻ የስፖርት ማዝወተሪያ ስፍራ ወይም የተለያዩ ከሆቴሉ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ኢቨንቶች ለሚያዘጋጁ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል፡
ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ቦታውን በራሳቸው ወጪ በማልማት መከራየት ይችላሉ።

  • የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ ፤
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት (VAT) ያላቸው፤
  • የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፍኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
  • ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደረግ 10 (አስር) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ለ"ገነት ሆቴል" በሚል በማሠራት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ቦታውን በአካል ተገኝተው በማየት 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ እና 10% የአገልግሎት ክፍያን ጨምሮ በጥቅል ቦታውን በወር የሚከራዩበትን ዋጋ በመግለጽ ቴክኒካል መስፈርቱንና ፋይናንሱን ለየብቻ በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ, ገነት ሆቴል አስተዳደር ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን እስከ አሥረኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደር ክፍል ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፤ አሰረኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል።
  • አንድ ተጫራች መጫረት የሚችለው በአንድ የጨረታ ሰነድ ብቻ ነው፡፡

ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ካሳ ግራንድ ሞል ፊት ለፊት
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-0115-504701/0911-250641/0939-500000

በሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት የገነት ሆቴል

✨ messages.ai_summary
Genet Hotel seeks to lease open spaces in its compound for a children's playground and sports area, or for events related to the hotel. Bidders must develop the site at their own expense and hold a renewed business license, VAT registration, and TIN.
Save Tender