Tender Detail

Tender Details

  • Company የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ
  • Address AMHARA Ethiopia, Phone: ------
  • Website
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300(ሶስት መቶ ብር)
  • Bid Securityለሎት 1፡2፡3 እና 6 ለእያንዳንዳቸው ብር 300,000.00/ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ፣ለሎት 5 ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ለሌሎች ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና
  • opening dateበቀን 01/03/2019 ዓ/ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • Categories Catering And Cafeteria Services , Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ በኮሪደር ልማት የተገነቡ የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎችና ሱቆችን ለማከራየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የኮንትራት የኪራይ አገልግሎት ውል መውሰድ ይፈልጋል፡፡

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ


ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተልማት መምሪያ በኮሪደር ልማት የተገነቡ የተለያዩ የመዝናኛ ቦታዎችና ሱቆችን ለማከራየት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊው ድርጅት ጋር የኮንትራት የኪራይ አገልግሎት ውል መውሰድ ይፈልጋል፡፡

  • "ዙብል ፓርክ" ፋዉንቴን፣ የተሟላ የህፃናት መጫወቻ፣ ከቤት ዉጭ የቡና መጠጫ ያለው (Outdoor Coffee Shop)፣ የካፌ እና የሬስቶራንት አገልግሎት እና የመዝናኛ ቦታ በሎት 01
  • በ"ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ የጅም አገልግሎት መስጫ እና ደረጃውን የጠበቀ የሞሮጫ መም (Running track) በሎት 02
  • "ዙብል ፓርክ" ቁጥር 2 ዙብል ፈረስ፣ ፋዉንቴኖች ያሉበት፣ ከቤት ውጭ የቡና መጠጫ ቦታዎች (Outdoor Coffee Shops) ያሉት፤ ለሰርግ እና ለተለያዩ ፕሮግራሞች ምቹ የሆነ መናፈሻ ያለው፣ የካፌ አገልግሎት መስጫ እና የመዝናኛ ቦታ በሎት 03
  • አብዮት አደባባይ ቁጥር 1 ፋውንቴን ያለው የካፌ እና የመዝናኛ አገልግሎት በሎት 04
  • አብዮት አደባባይ ቁጥር 2 ከቤት ውጭ የካፌ አገልግሎት በሎት: 05
  • ጎንደር መምህራን ኮሌጅ መግቢያ በር በቀኝ በኩል እስከ "የአርበኛ ልጅ" የፓርኪንግና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ቻርጅ አገልግሎት መስጫ ያለው የካፌ አገልግሎት እና የመዝናኛ ቦታ በሎት 6
  • በ "ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 21 ካሬ የሆነ ሱቅ ቁጥር 1 በሎት 7
  • በ "ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 35 ካሬ የሆነ ሱቅ ቁጥር 2 በሎት 8
  • በ "ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 35 ካሬ የሆነ ሱቅ ቁጥር 3 በሎት 9
  • በ"ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 25 ካሬ የሆነ ሱቅ ቁጥር 4 በሎት 10
  • በ"ዙብል ፓርክ" ውስጥ የሚገኝ ስፋቱ 27 ካሬ የሆነ ሱቅ ቁጥር 5 በሎት 11

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘመኑ የታደሰ በዘርፉ የሚመለከተው ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ : ከላይ ከተ.ቁ 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣
  4. ስለመዝናኛ ቦታዎችና ሱቆች አጠቃላይ መረጃ እና ስለሚሰጡት የአገልግሎት አይነት ዝርዝር መግለጫቸው /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከ21/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ እስከ 30/02/2019 ዓ/ም ድረስ ለ10 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰአት የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር / በመክፈል ከጎንደር ከተማ አስ/ከተማ እና መሰረተልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 21 ሰነዱን መግዛት ይቻላሉ፤
  6. ተጫራቾች ከመዝናኛ ቦታዎች ከሁሉም ሎቶች የሚፈልጉትን ሎት መርጠው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን ከአንድ ሎት በላይ መጫረት አይችሉም፡፡ ስለሆነም ከአንድ ሎት በላይ ለመጫረት ሰነድ ያስገባ ተጫራች ቢኖር ያለምንም ቅድመሁኔታ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 1፡2፡3 እና 6 ለእያንዳንዳቸው ብር 300,000.00/ሶስት መቶ ሺህ ብር/ ፣ለሎት 5 ብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) ለሌሎች ሎቶች ለእያንዳንዳቸው ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከፖስታው ውስጥ ማስገባት አለባቸው፣
  8. ጨረታው ከ21/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳባቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ከጎንደር ከተማ አስ/ከተማ እና መሰረተልማት መምሪያ ቢሮ ቁጥር 23 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 01/03/2019 ዓ/ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም በመምሪያው ግዥና ፋ/ንብረት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር-23 በቀን 01/03/2019 ዓ/ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ የሚለየው በተወዳደረበት ሎት ለወርሃዊ ኪራይ አገልግሎት በሞላው ከፍተኛ ዋጋ ነው፡፡
  11. ማንኛውም ተጫራች በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለበት ከውድድር ውጭ ይደረጋል፤
  12. የጨረታ አሸናፊው ለመዝናኛ አገልግሎት የሚያስፈልጉ ቦታውን የሚመጥኑ ጥራት ያላቸውን ሌሎች ተጨማሪ ግብአቶችን አሟልቶ ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ጥራታቸውም መ/ቤቱ በሚመድበው ባለሙያ አማካኝነት የሚፈተሽ እና የሚረጋገጥ ይሆናል፡፡
  13. ለአሸናፊ ድርጅቱ እንደአስፈላጊነቱ ሊራዘም የሚችል የሁለት(2) አመት የኪራይ አገልግሎት ውል የሚሰጠው ይሆናል፡፡
  14. ነጻ የህዝብ አገልግሎት እንዲሰጡ የተገነቡ ክፍት የመዝናኛ ቦታዎች ባሉበት ሎት (ሎት 04 እና 05) አሸናፊ የሚሆን ድርጅት ማህበረሰቡ ያለከፍያ የመዝናናት መብቱን ባከበረ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚገደድ ሲሆን የመዝናኛ ቦታውን ፅዳት እና አጠቃላይ ደህንነት በመጠበቅ በሃላፊነት ማስተዳደር ይጠበቅበታል፡፡
  15. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 23 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0918712038 ወይም በ 0996648851 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
  16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤ ሆኖም ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ላወጡት ወጭ መምሪያው ሀላፊነት የማይወስድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የጎንደር ከተማ አስ/ከ/መሰረተ ልማት መምሪያ
ጎንደር

✨ messages.ai_summary
Gondar City Administration invites bids to lease various recreational areas and shops built under corridor development, across 11 lots including Zubl Park fountain, children's playground, outdoor coffee shop, cafe/restaurant, running track, wedding/event venue, and shops of 21–35 sqm. Bidders need a valid trade license and tax ID, and may bid on only one lot.
Save Tender