የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር ኢፕድ 011/2019
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃዎች እና የአገልግሎት ግዥዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የንግድ ምዝገባ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
- የቫት ሰርተፍኬት
- በመንግሥት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ
ሎት-1. የአይሲቲ እቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 150,000 ( አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር)
ሎት-2 የጥናት አማካሪ አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን 15,000 (አስራ አምስት ሺህ ብር)
በሲ.ፒ.ኦ፣ ቢድቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
- ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 ሰአት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን፤ የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉለውም፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Press Agency seeks bidders for ICT equipment (Lot 1) and research consultancy services (Lot 2) via open tender. Eligible bidders need a valid trade license, business registration, TIN, VAT certificate, and government supplier registration. Bids go in four sealed envelopes (technical and financial, original and copy).
