የመኪና መለዋወጫ ዕቃ ግዥ (ሁለተኛ ዙር) - የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
የሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሁለተኛ ዙር የወጣ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000/አስር ሺህ/ ብር c.p.o/ሲ.ፒ.ኦ/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል፡፡
- በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በተጫራቾች መመርያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶክመንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ C.P.O (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ፣የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ስጪዎችን በራሱ ሽፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል
- ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100(አንድ መቶ )ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት አምስተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥኑ በ16 ኛው ቀን ከቀኑ 9:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ ማጫረት አይችልም፡፡
- የወቅቱን የገቢያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም፤ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0462125731 እና 0911746687 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
✨ messages.ai_summary
The Sidama National Regional State Peace and Security Bureau seeks to purchase vehicle spare parts through a second-round open tender. Bidders must submit trade license, business registration, tax identification and VAT registration certificates, plus a government supplier eligibility certificate.
