የደንብ ልብስ፣ የጽሕፈት፣ የትምህርት መርጃ፣ ፅዳት፣ የተሽከርካሪ፣ ጀኔሬተርና ማሽነሪ መለዋወጫ፣ የግንባታና የጋራዥ ዕቃዎች ግዥ (መከ/ሰ/ምስ/ዕዝ/ግ/ጨ/01/2019) - የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
በኢፌዱሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር መከ/ሰ/ምስ/ዕዝ/ግ/ጨ/01/2019
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት ለዕዙ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ የጽሕፈት ዕቃዎች፣ የትምህርት መርጃ ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳትና ሌሎች አቅርቦቶች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ የጀኔሬተር መለዋወጫ፣ የዳቦ ማሽን መለዋወጫ፣ የማሽነሪ መለዋወጫ ዕቃዎች እና አላቂ የጋራዥ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ሁኔታዎች፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ አቅራቢዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡና በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ጨረታው የሚከናወነው በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ባወጣው የመንግሥት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 500.00/ አምስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል የተሟላና በአማርኛ የተዘጋጁ ሰነዶችን በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ማግኘት ይችላሉ። የጨረታው ሰነድ የሚላከው በተጫራቾች ወይም በሕጋዊ ወኪሎቻቸው ሲሆን ሰነዱ ቢጠፋ ወይም ቢዘገይ ኃላፊነቱን የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች ተ.ቁ 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ከጥቅምት 17 ቀን 2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ድረስ ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች በተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ከታወቀ ባንክ በሲ.ፒ.ኦ ከሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ፋይናንሻልና ቴክኒካል እንዲሁም ኦርጅናልና ኮፒ ማስታወቂያው አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተራ ቁጥር 6/ሀ/ በተገለፀው አድራሻ ጥቅምት 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይከፈታል።
- ለተጨማሪ ማብራሪያና ሰነድ ማስገቢያ፡-
- ሀ/ ተጫራቾች ለሚኖራቸው ጥያቄ፡- ዘወትር በሥራ ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሠመራ ከተማ የሰሜን ምስ/ዕዝ/ፋ/ሥ/ሥራ አመራር ግዥ ክፍል ቢሮ በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር፡ -0991454479/0939055793 መጠየቅ ይችላሉ።
- ለ/ የሰነዱ ሽያጭ የሚከናወንበት አድራሻ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ።
- ሐ/ ጨረታው የሚላክበት አድራሻ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ።
- መ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ፡- በተ/ቁ 6/ሀ/ ላይ ይመልከቱ።
- ሠ/ ንብረቱ ገቢ የሚሆነው፡- ሠመራ ከተማ የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ንብረት ግ/ቤት ነው።
ዕዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ጠ/መምሪያ
✨ messages.ai_summary
The North East Zone Procurement Directorate of Ethiopia's Ministry of Defense seeks suppliers for uniforms, office and educational supplies, cleaning materials, vehicle, generator, bakery machine and machinery spare parts, construction materials, and garage consumables via open national tender. Bidders must hold a valid trade license, tax clearance, VAT registration, and be registered on the government suppliers list.
