Tender Detail

Tender Details


የጽሕፈት፣ የዩፒቪሲ፣ የደንብ ልብስ፣ የፅዳትና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ - በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ

በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ


የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ በ2019 የበጀት ዓመት የጽሕፈት እቃዎች ፣ የዩ.ፒ.ቪ.ሲ ዕቃ ፣ የደንብ ልብሶች ፣ የፅዳት ዕቃዎች እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለፀውን መመሪያ በመከተል ከዚህ ጋር ተያይዞ በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲሳተፉ ታጋብዘዋል፡፡ [ከፎቶው በከፊል የማይነበብ]

የጨረታ መመሪያ፡-

  1. ተጫራቾች በ ጨረታ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና ግብር መክፈላቸውን የሚገልፅ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጂናልና ኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች ሰነዱን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 500/አምስት መቶ/ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ለያንዳንዱ ሎት በ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ እና ባንክ ጋራንት /An unconditional Bank Guarantee/ማስያዝ አለበት፡፡
  5. ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን 4:00 ሰአት ላይ ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን ከጠዋቱ 4:30 ባለቤቱ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታው ሳጥን ይከፈታል። በእለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ሙሉ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን ፣የድርጅ ታቸውን ማህተም በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች 3% ዊዝሆልዲንግ መክፈል አለባቸው፡፡
  8. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የተፃፈ መሆን አለበት፡፡
  9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ጨረታው ላይ ሲቀርብ /ለመሳተፍ /ሙሉ የኦዲት ሪፖርት የ2018 ዓ.ም ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይ ጊዜ (Price Validity date) ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ የሚጸናበትን ጊዜና ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበት ጊዜ 120 /አንድ መቶ ሀያ/ ቀናት (Delivery time) ውስጥ ማስረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
  11. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልቶ ካልቀረቡ ና ማንኛውንም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ኃላፊነቱን የ አቅራቢው ድርጅት ነው፡፡
  13. ድርጅቱ የሚያጫርታቸውን እቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ይችላል፡፡
  14. የዕቃዎቹ ዋጋ የሚከፈለው ዕቃዎቹ በግምጃ ቤታችን ገቢ ከሆኑ በኋላ ነው፡፡
  15. የሚቀርበው ዋጋ በሙሉ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
  16. ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች አቅራቢው ድርጅት በራሱ ትራንስፖርት መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
  17. ከዚህ በላይ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ሳይወጡ ወይም ውሉን በ አግባቡ ሳይፈፅሙ ቢቀር ለውል ማስከበሪያ ዋስትና የተያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤቱ ገቢ ይሆናል እንዲሁም አስፈላጊ የህግ ትጥቃቱንም የሚቀበል ይሆናል።
  18. ተጫራቹ የጽዳት እቃዎችን፣ ለደንብ ልብሶች እና የዪ.ጉ.ዪ ዕቃዎች ላይ ለ እያንዳንዱ እቃ የእቃ ዓይነት ላይ በተጠየቀው መሠረት ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡
  19. ለኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ላይ የዕቃው ካታሎግ መቅረብ አለበት፡፡
  20. ተጫራቹ ከሁን በፊት በጨረታ ከተሳተፉባቸው የመንግስትና የግል ድርጅቶች የዕውቅና ሠርተፊኬት ማቅረብ አለበት፡፡
  21. በጨረታው ለማገር የቀረቡ እቃዎች በሙሉ ጋራንትድ መሆን አለባቸው ፡፡
  22. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው 50000/ሀምሳ ሺ/ብር እና ባንክ ጋራንት /Anunconditional Bank Guarantee አሸናፊው አካል ዕቃውን አስገብቶ እስኪጨርስ ድረስ የማይመለስ መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
  23. ያሸነፈው ተጫራች የውል ማስከበሪያ 10% ለውል ማስከበሪያ ያሲዛል፤ እቃውን ሙሉ በሙሉ የማያቀርብ ከሆነ የውል ማስከበሪያው የማይመለስ ይሆናል።
  24. ተጫራቹ በዪ.ጉ.ዪ ዕቃዎች ላይ ካሸነፈ የውሃ ፈንድ/Wetr Fund/ 0.5% የሚከፍል ይሆናል፡፡

በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሱሉልታ ቅርንጫፍ

✨ messages.ai_summary
Sheger City Water & Sewerage Service, Sululta Branch, invites bids for stationery, UPVC items, uniforms, cleaning supplies, and electronics per attached specifications. Bidders need a valid trade license, tax and VAT registration, supplier registration, and tax clearance. Samples are required for cleaning supplies, uniforms, and UPVC items; catalogs for electronics.
Save Tender