Tender Detail

Tender Details


የደረቅ ምግብ፣ ሳሙና፣ ዲጂታል ሳይኔጅ፣ ቪዲዮ ዎል ፍሬም፣ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ ሞተር ሳይክሎች፣ የሳር አጨዳ እና ያገለገሉ ዕቃዎች ሽያጭ (8 ምድብ) - ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

Hamlin Fistula Ethiopia (ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ በወሊድ ወቅት ችግር የሚገጥማቸውን እናቶች ከስድሳ አመታት በላይ የነፃ ሕክምና እየሰጠ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን፣ ከነፃ ሕክምናው በተጨማሪ በሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ት/ቤት በመጀመሪያና በሁለተኛ ዲግሪ፣ እንዲሁም በቡራዩ ልዩ ዘን በሚገኘው የደስታ መንደር መልሶ ማቋቋም ማዕከል፣ በምንሰጠው ሕክምና ሌሎችና ተጨማሪ የቀርብ ክትትል ለሚያስፈልጋቸው እናቶች የራስ-አገዝ የሙያ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

በዚሁም መሠረት ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ ቀጥሎ በተዘረዘሩት ምድቦች ግዢ በሚፈፅምባቸው ልዩ ልዩ መገልገያዎች እና አገልግሎቶች ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶችን በዚህ ማስታወቂያ ይጋብዛል፡፡

  • ምድብ ሀ:- በአዲስ አበባ ፊስቱላ ሆስፒታል ተኝተው ለሚታከሙ ህሙማን እና በሐምሊን አዋላጅ ነርሶች ት/ቤት ስልጠናቸውን ለሚከታተሉ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የደረቅ ምግብ እና የባልትና ውጤቶች አቅርቦት፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ ለ:- ለድርጅቱ አገልግሎት የሚውሉ የደረቅ እና አሸን ሳሙና/HARD SOAP & POWDERED DETERGENT/ ግዢ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ ሐ:- ድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያን የሚገልፅ ሁለት የማስተዋወቂያ ስሌዳዎች/DIGITAL SIGNAGE/ ሥራ እና ተከላ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ መ:- በሐምሊን የአዋላጅ ነርሶች ት/ቤት የማስተማሪያ ክፍል/LECTURE HALL/ ለሚገጠም አዲዮ- ቪዥዋል ስክሪን የሚያገለግል በቂ አቅም ያለው የብረት ፍሬም ተከላ /VIDEO WALL STRUCTURAL ARRAY/፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ ሠ:- በባህርዳር የሐምሊን ፊስቱላ ማዕከል ለሚካሄደው ጥልቅ የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ እና ከድርጅቱ የውሃ ሥርጭት መስመር ጋር የማገናኘት ሥራ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 400.00/አራት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ ረ:- የድርጅታችን ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ አጋር ከሆኑ የመንግስት ጤና ተቋማት ጋር በጋራ እየተተገበረ ላለው የፕሮጀክት ዜሮ አገልግሎት የሚውሉ ስድስት/06/ የሞተር ሳይክሎች ግዢ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/፣
  • ምድብ ሰ:- በደስታ መንደር የመልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል ግቢ ውስጥ ያለውን የግጦሽ ሳር አጭደው ድርጅታችን በሚፈልገው መልኩ በባንዳ አስረው የሚያስረክቡ ድርጅቶች፣ የሰነድ ግዢ የለውም፣
  • ምድብ ሸ:- በደስታ መንደር መልሶ ማቋቋሚያ ማዕከል የሚገኙ እና በሰባት/07/ ምድቦች የተለዩ፣ አገልግሎት ላይ ውለው የሚወገዱ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እና የመኪና ጎማዎች ሽያጭ፣ የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር ብቻ/ ፡፡

ተጫራቾች ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዳቸው ምድቦች የተዘጋጁትን ሰነዶች በየምድቦቹ አንፃር የተገለፀውን የሰነድ ክፍያ በመፈፀም ከሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡

የምድብ ሀ፣ ለ፣ መ፣ ረ፣ እና ሰ ጨረታ እስከ ማክሰኞ ጥቅምት 24፣ 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን (ጥቅምት 24፣ 2018ዓ.ም) ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል፣

የምድብ ሐ፣ ሠ፣ እና ሸ ጨረታ እስከ ኅዳር 1፣ 2019ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰአት ድረስ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማብቂያው ቀን ከቀኑ 8:30 ሰዓት ይከፈታል፣

ከላይ የተዘረዘሩትን የጨረታ ምድቦች በከፊል ወይንም በሙሉ ለመሰረዝ ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡

ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ
ስልክ ቁጥር +251-113716544/45/46-የውስጥ መስመሮች 139/182፣ በተጨማሪም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹ ላይ በተገለፁት የስልክ ቁጥሮች ደውለው የሚያስፈልጋቸውን ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ

Hamlin Fistula Ethiopia - ሐምሊን ፊስቱላ ኢትዮጵያ

✨ messages.ai_summary
Hamlin Fistula Ethiopia invites bids across 8 lots: dry food and bakery products; bar and powdered detergent; digital signage supply and installation; video wall structural array for a lecture hall; deep water well drilling and connection to the water line in Bahir Dar; six motorcycles for project field service; grass cutting and baling at Desta Mender; and sale of used equipment and tires.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender