Tender Detail

Tender Details

  • Company Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-558-2660
  • Website
  • Deadline10 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazinereporter
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Security200,000.00
  • opening dateህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Labour Outsourcing Services

አማራ ባንክ አ.ማ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ለከፈታቸው ቅርንጫፎች ከዚህ በታች የተገለፀውን አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመለየት ውል ስምምነት ፈፅሞ ማሰራት ይፈልጋል::

Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)


አማራ ባንክ አ.ማ

Amhara Bank S.C.

ሀገር አቀፍ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- አባ/ሰቼፋማ/ሀግጨ/053/2026

(1) አማራ ባንክ አ.ማ አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በሁሉም የሃገሪቱ አካባቢዎች ለከፈታቸው ቅርንጫፎች ከዚህ በታች የተገለፀውን አገልግሎት የሚያቀርቡ ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመለየት ውል ስምምነት ፈፅሞ ማሰራት ይፈልጋል::

የአገልግሎት ዓይነትጨረታው የሚዘጋበት ቀንና ሰዓትጨረታው የሚከፈትበት ቀንና ሰዓትየጨረታ ማስከበሪያ
የፅዳት ሰራተኛ አገልግሎት አቅራቢ ድርጅትህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓትህዳር 01 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:30 ሰዓት200,000.00

(2) ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከለገሃር ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም በሚወስደው መንገድ መብራቱን እንደተሻገሩ ከአመልድ ህንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ሰፕላይ ቼይን እና ፋሲሊቲዎች አስተዳደር መምሪያ 20ኛ ፎቅ ላይ ከጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀናት (ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት በኋላ ከቀኑ 7:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11:00 ሰዓት በተጨማሪም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ) የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ::

(3) ተጫራቾች ከጨረታው በኃላ የሚመለስ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ከላይ በተገለፀው መሠረት ከጨረታው መክፈቻ ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲፒኦ ወይም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሚሰጥ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአማራ ባንክ አ.ማ. ስም አሰርተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

(4) ተጫራቾች የሙያ ፈቃድ፣የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ እና ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

(5) ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት መሠረት ማስገባት አለባቸው:: ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም::

(6) የጨረታው ሰነድ አማራ ባንክ አ.ማ. 20ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የሰፕላይ ቼይን እና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት መግባት ይኖርበታል::

(7) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት አማራ ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ግዥና ፋሲሊቲ መምሪያ 20ኛ ፎቅ ይከፈታል::

(8) ከላይ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች አለማሟላት ከጨረታው ውጭ (ውድቅ) ያስደርጋል::

(9) ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-29-05 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::

(10)ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

Amhara Bank S.C.
Beyond Financing

✨ messages.ai_summary
Amhara Bank seeks cleaning/janitorial and labour outsourcing providers to serve its branches across Ethiopia, including Addis Ababa, under a framework contract. Bidders must submit professional licence, renewed business licence, registration certificate, taxpayer and VAT certificates, and tax clearance.
Save Tender