Tender Detail

Tender Details

  • Company የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
  • Address , Phone: 011 1320 090
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 5:30 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 3:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት


የሊዝ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በሚደነግገው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 መሰረት በ2019 በጀት ዓመት ለ1ኛ ዙር ጨረታ ለመኖሪያ እና ንግድ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በጨረታ ለተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡

  1. በመሆኑም መጫረት ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቦታውን ዝርዝር መረጃና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11:00 ሰዓት ድረስ ይሆናል፡፡
  3. ጨረታው የሚዘጋው በአስረኛው ቀን 11:30 ላይ ይሆናል፡፡
  4. ጨረታው የሚከፈተው ከተዘጋበት ቀን ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 3:00 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ በተመለከተ በዓ/ከ/ከ/አስ/መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በዓ/ከ/ከ/አስ/መሬት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  6. የጨረታውን ዝርዝር መረጃ በጽ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ መለጠፊያ ሰሌዳ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡
  7. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ :- ዓለምከተማ ስልክ ቁጥር 011 1320 090

የዓለም ከተማ ከተማ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Alem Ketema Town Administration Land Office invites bids for urban land plots for residential and commercial use under Lease Proclamation No. 721/2004, Article 8(1). Open to any person or organization; bid documents available at the office. The office reserves the right to cancel the tender in part or fully.
Not stated in the notice: bid security. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender