Tender Detail

Tender Details


የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮና የትምህርት፣ የጽዳት፣ ልዩ ልዩና ቋሚ እቃዎች እና የኤሌክትሮኒክስና ማሽነሪ ጥገና ግዥ (7 ሎት) - አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

ትምህርት ቤታችን ማለትም አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የትምህርት ግብአቶች ለመሟላት እና ምቹ የትምህርት አሰጣጥ ለማጎልበት ውጤታማ ህብረተሰብ ለመፍጠር እንዲሁም ግልጸኝነትና ጥራት የጠበቀ መልካም አገልግሎት ለመስጠት ኪራይ ሰብሳቢነት ለመቀነስ እና ጠንካራ የልማት ሰራዊት ለመፍጠር ነው፡፡

የጨረታው ግብአቶች:-
አቃ/ቃ/ከ/ከተማ አስተዳደር አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ /መ/የመ/ ደ /ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ዝርዝር ማለትም፡-

  1. የደንብ ልብስ ----- 36000.00 (cpo)
  2. አላቂ የቢሮ እቃዎች---------9000.00 (cpo)
  3. አላቂ የትምህርት እቃዎች---9000.00 (cpo)
  4. የጽዳት እቃዎች--------32000.00 (cpo)
  5. ልዩ ልዩ እቃዎችና ---------3000.00 (cpo)
  6. ኤሌክትሮኒክ እና ማሽነሪ ጥገና----2000.00 (cpo)
  7. ቋሚ እቃዎች-------14000.00(cpo)

ት/ቤቱ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ አነዚህን እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ሊያሟሉ የሚገባቸው መስፈርቶች እንደሚከተለዉ ይሆናል ፡፡

  • የመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግቦ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  • የዘመኑ ግብር የከፈሉና ማስረጃ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር )በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው ዋጋ ማቅረቢያ ላይ ሞልቶ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2:30 እስከ 11:00 በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ለተሸናፊው የስያዙትን ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡
  • ጨረታውን ለማባዛት መሞከር ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ጨረታው ማስከበሪያውም እንደሚወረሱ ማወቅ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ ማስገባት አለበት፡፡
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ተዘግቶ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 5:00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  • በማንኛውም የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፉ ያልታገዱ፡፡
  • ተጫራቾች የእቃዎች ናሙና ከየአይነቱ ጨርቅ ከሆነ 2ሜትር ያልበለጠ እና ቋሚ እቃ ከሆነ በፎቶ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታ ሳይዘጋ በፊት አንድ አንድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪም ት/ቤቱ በሚያቀርበው ናሙና ይፈጸማል፡፡ የጨረታው ውጤት ከታወቀ በኋላ የቀረቡት ናሙናዎች ለተሸናፊዎች ሲመለሱ የአሸናፊው ተጫራች ናሙናዎች ግን አይመለስም፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ሲያቀርብ ዋናውንና ቅጂውን በሚመለከተው መፈረምና ማህተም መደርግ አለበት፡፡
  • ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ላይ የሚሞሉትን በመሙላት እያንዳንዱ ቅጽ ላይ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ምንም ሳይጨምር ሳይቀንስ መመለስ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
  • ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብ ወይም ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውን አድራሻቸውን እንዲሁም ስልክ ቁጥራቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ዊዝሆልዲግ ታክስ ከአሸናፊ ድርጅት ይቆረጣል፡፡
  • የርክክቡ ቦታ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ እቃው በንብረት ክፍል ካስገባና ጥራቱን ከተረጋገጠ በኋላ ክፍያ ይፈጸል፡፡
  • ከጥቃቅንና አነስተኛ ወይም ከአደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ ምንም አይነት ምርት እንደማያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ የሚስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የአገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ /ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራቹ የተሰጣቸውን ፍቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

አድራሻ :-አቃቂ ቃሊቲ ገላን ኮንዶሚኒየም ገላን ከጤና ጣቢያ ወረድ ብሎ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ብለው ይጠይቁ፡፡

ማሳሰቢያ:-የጨረታ ሰነዱን ስታስገቡ ሙሉን ሰነድ ሳይቆራረጥ ኦርጅናሉ እና ኮፒውን በ2 ፖስታ አሽገው ሊቀርቡ ይገባል፡፡ ማስገቢያ ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 6 ይሆናል፡፡

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ የመ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Artist Hachalu Hundessa Memorial Primary School seeks suppliers for uniforms, consumable office and educational supplies, cleaning materials, miscellaneous and fixed assets, and electronics/machinery maintenance, in 7 lots. Bidders must be registered government suppliers, VAT-registered, have a renewed business license, and provide tax payment evidence. Samples required.
Save Tender