የፅህፈት፣ የፅዳት፣ ልዩ ልዩ፣ ቋሚ፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የህክምናና የትምህርት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስና የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ግዥ (9 ሎት፣ 001/2019) - ለሚ ኩራ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ ደ/ት/ቤት
የግዥ ግልፅ ጨረታ ማሰታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ /ደ/ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለስራ የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን ማለትም ሎት1:- የፅህፈት ዕቃዎች፣ ሎት 2:- የፅዳት ዕቃዎች ፤ሎት 3:- ልዩልዩ እቃዎች ሎት 4:- የደንብ ልብስ ሎት 5 :-የቋሚ እቃዎች ሎት 6:- ኤሌክትሮኒከስ ፤ ሎት 7:- የህክምና እቃዎች ሎት 8 :-ኤሌክትሮኒከስ ጥገና 9:- የትምህርት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብ ርለመከፈላቸው ማስረጃማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራች ከዚህበታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.P.O. ማቅረብ አለበት፡፡
ሎት ቁጥር የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር ሎት 1. የጽህፈት እቃዎች ብር 74000 ሎት 2. የፅዳት እቃዎች ብር 68000 ሎት 3. ልዩልዩ እቃዎች ብር 20000 ሎት 4. ደንብ ልብስ ብር 60000 ሎት 5 . ቋሚ እቃዎች ብር 28000 ሎት 6 . የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ብር 30000 ሎት 7 . የህክምና እቃዎች ብር 10000 ሎት 8. ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ብር 29000 ሎት 9. የትምህርት እቃዎች ብር 33000 - የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር100(አንድ መቶ) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 05 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር ) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዘጊያናመክፈቻ የስራቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራቀን በተሰጠው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት መስሪቤቱ ድረስ ማቅርብ አለበት፡፡
- መ/ቤ/ቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስምሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- መ/ቤ/ቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ_ስልክ 0118681536 / 0118681537
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ስሙ መሪ ገበያ 500 ሜትር ገባብሎ ይገኛል፡፡
አዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 መሪ የመጀመሪያ /ደ/ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Meri Primary School in Addis Ababa (Lemi Kura, Woreda 10) seeks legal suppliers for 9 lots: stationery, cleaning supplies, miscellaneous items, uniforms, fixed assets, electronics, medical supplies, electronics repair, and educational materials. Bidders need a valid business license, supplier registration, renewed trade license, and VAT certificate.
