Tender Detail

Tender Details

  • Company በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት
  • Address , Phone: ..........
  • Website
  • Deadline06 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceብር 500 (የማይመለስ)
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ × ካሬ፡ ለመኖሪያ 80%፣ ለድርጅት 50% (CPO)
  • opening date30/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት
  • Categories Land , House, Building And Warehouse

19ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ (ለንግድና ለመኖሪያ) - በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት


የመሬት ሊዝ የጨረታ ማስታወቂያ

  1. የጨረታው ዙር ---19ኛ
  2. የጨረታው አይነት ____________መደበኛ
  3. የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ የሚደነግገው አዋጅ 721/2004 አንቀፅ 8 ንዑስ አንቀፅ 1 ይህንኑ አዋጅ በማስፈጸም የአብክመ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ቢሮ የከተማ ቦታን በሊዝ ስለማያዝ በወጣው ደንብ ቁጥር 103/2004 በክፍል 3 በአንቀፅ 10 በንዑስ አንቀፅ 1 በፊደል ተራ ከ "ሀ" እስከ "ሠ" በተዘረዘረው መሰረት ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች ማለትም ለንግድ አገልግሎት እና ለመኖሪያ አገልግሎት የሚውሉ ቦታዎችን በግልፅ ጨረታ በተጫራቾች ማስተላለፍ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም መጫረት የሚፈልግ ግለሰብ ወይም ድርጅት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የቦታው ዝርዝር መረጃ እና የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል በሸ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 24 ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ ሰነድ ላይ በቀረበው መሰረት መሆን ይኖርበታል፡፡
  5. ተጫራቾች ሁለት የተለያዩ ፖስታዎችን በማዘጋጀት ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውስጥ በመለየት ክፍል ሁለት የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱን እና ክፍል ሦስት የጨረታ ሀሳብ ማቅረቢያ ሰነዱን እንዲሁም ሲፒኦን ሁለቱን ሰነዶች አንዳንድ ኮፒ በማድረግ ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን በብቻ በተለያዩ ፖስታዎች በሰም ወይም በአካባቢው በሚገኝ ማጣበቂያ በማሸግ እና ፖስታዎቹ ላይ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለይቶ በመፃፍ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ15/2/19ዓ.ም ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ፖስታውን እስከ 10ኛው /አስረኛው/ ቀን 11:00 ሰዓት ማለትም 27 /2/19 በከተማ አስተዳደሩ ለጨረታ ተግባር በተዘጋጀው ቦታ ኦርጂናሉን ሰነድ በዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እና ኮፒውን ሰነድ ደግሞ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
  6. ጨረታው የሚዘጋው ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት 15/2/19 ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን 27/02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 11:00 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
  7. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ 3:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  8. ጨረታው ተጫራች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሸ/ከ/አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የሥራ ቀን 30/02/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
  9. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ እና በጽ/ቤት ማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ እንዲሁም የሸ/ከ/አስ/መሬት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 27 ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለመኖሪያ የመነሻ ዋጋውን በካሬ ተባዝቶ 80 ፐርሰንት ማነስ የለበትም፡፡
  12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ለድርጅት የመነሻ ዋጋውን በካሬ ተባዝቶ 50 ፐርሰንት ማነስ የለበትም፡፡

ማሳሰቢያ:- በግልጽ የማይነበቡ ስርዝ ድልዝ ያለባቸው ሰነዶች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን የሸ/ከ/ አስተዳደር መሬት ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
The She/Ke administration Land Office in North Wollo Zone invites bidders to a 19th-round open land lease tender for commercial and residential plots. Individuals or organizations may buy the tender document and site details. Bids must follow the instruction document and be submitted in two separately sealed envelopes (original and copy). The office may cancel the tender in part or in full.
Save Tender