በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀ/ደ/ት/ቤት ለ 2019 ዓ.ም ዓመት በጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 8 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀ/ደ/ት/ቤት ለ 2019 ዓ.ም ዓመት በጀት አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ማሠራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1. ቋሚ እቃ 2000 ሎት 2. የደንብ ልብስ እና የስፌት አቅርቦት 3000፣ ሎት3. የፅዳት እቃዎች 2500፣ ሎት 4. የፅሕፈት መሣሪያዎችና አላቂ የቢሮ እቃዎች 2000 ሎት 5. የስፖርት ማቴሪያል እቃ 1000፤ ሎት 6. የህትመት ውጤቶች 1000፤ ሎት 7. የሕክምና እቃዎችና መድሃኒት 1000 ሎት 8 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች 1000፤ ሎት 9 የግንባታ እቃዎች 1000፤ ሎት 10 ለፕላንት ለማሽነሪ ጥገና እና እድሳት 1000፤ ሎት 11 ለመስተንግዶ የሚሆን አቅርቦት (ውሃ ቆሎ...) 500 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ለመግዛትና ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በጨረታ ለመወዳደር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የምዝገባ ፍቃድ የዘመኑ ግብር የከፈሉና ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት (Tax) ተመዝጋቢ የሆኑና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማንኛውንም የመንግሥት ታክስና የግብር ግዴታዎች ከመጓጓዣው በሚያቀርቡበት የመወዳደሪያ ነጠላ ዋጋ ውስጥ አካተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታ ማስከበሪያ በዳግማዊ ቴዎድሮስ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ በተረጋገጠ ከ 05-2% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል በግንባር በማቅረብ ለዚሁ የተዘጋጀውን ሰነድ ብር 200 ብር በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን እቃ ሳንፕል ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው ሳንፕል ለማይቀርብባቸው የቋሚ የዕቃ አይነቶች ት/ቤቱ በሚያቀርበው እስፔሲፊኬሽን መሰረት መሙላትና የፎቶ ሳንፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል ፡፡
- በጥቃቅንና አነስተኛ ለሚመጡ ተጫራቾች ማምረት በሚችሉበት ብቻ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ማምረት በማይችሉበት እቃዎች የጨረታ ሰነድ እንደ ማንኛውም ተጫራች ገዝተው መወዳደር ይችላሉ፡፡ ከተደራጁበት ተቋም (መንግሥታዊ) የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የምዝገባ ፍቃድ፣ ቫት፣ ቲን፣ የዘመኑ ግብር የከፈሉ፣ ንግድ ፍቃዳቸውን ያደሱና የዋጋ ዝርዝራቸውን አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻል አንድ ቴክኒካል አንድ ኮፒና የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ሦስቱም በተለያዩ ፖስታዎች ለየብቻ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሙሉ የጨረታውን ሰነድ በመሙላትና በማሸግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ሙሉ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ማድረግ ይኖርባቸዋል ሙሉ የጨረታ ሰነድ ተመላሽ ያላደረገ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ለተከታታይ 10 የሥራ ቀን አየር ላይ ይውላል በቀጣዩ ቀን 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን በት/ቤቱ ቤተ/መፅሐፍት ከጠዋቱ 4:30 ላይ ይከፈታል ተጫራቾች ጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ ጨረታው ይከፈታል፡፡ ቀጣዩ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ወጪ ትምህርት ቤቱ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን የሕክምና ዕቃ በባለሙያ ታይቶ የሚገባ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃውን ከማስገባቱ በፊት ከት/ቤቱ ጋር ውል በሚፈፀም ውል ማስከበሪያ የዕቃውን 10% በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል ፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሑፍ በደብዳቤ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ አሸናፊው ድርጅቶች አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለጸለት በኋላ በሰባተኛው ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት፡፡
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ሊስት ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ-ገጽ WWW.pagov.et ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
አድራሻ፡- ከአዲስ ከተማ መሰናዶ ት/ቤት ፊት ለፊት 200 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፤ - በስልክ ቁጥር 0112- 130608 ደውለው መጠየቅ ይችላል
የዳግማዊ ቴዎድሮስ መጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት
✨ messages.ai_summary
Dagmawi Teodros Primary School seeks suppliers for 11 lots including fixed assets, uniforms and sewing supplies, cleaning materials, stationery and consumable office items, sports materials, printed materials, medical supplies and medicines, consumable educational materials, construction materials, plant and machinery maintenance, and catering supplies. Bidders must hold valid registration, TIN, and VAT registration, and submit samples or photo samples.
