በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር የ107ኛ ኮማ/ክ/ጦር 01/2019
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 የተለያዩ የፅህፈት እና የስልጠና ዕቃዎች
- ሎት 2 የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች
- ሎት 3 የህሙማን ማገገሚያ ዕቃዎች
ስለዚህ በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ድርጅቶች -
- ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዘርፍ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር(TIN)፣ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ያላቸው እና የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለጸው ብር መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) ወይም የባንክ ጋራንቲ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ለአንድ ሎት በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታውጆ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን ውስጥ ባሉት የስራ ቀናት በኦሮሚያ ክልል አልጌሪማ ወረዳ ወንዶጢቃ ካምፕ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር የግዥ ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ከጥቅምት 13 ቀን 2019 ዓ/ም እስከ ጥቅምት28 ቀን 2019 ድረስ ግዥ ክፍል ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ጥቅምት 28 ቀን 2019 ዓ/ም ከረፋዱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ በሚገኝ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር:- 09-10-31-80-43 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
NB ማስታወቂያ ጨረታው የሚወጣበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
በኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ የ107ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር
✨ messages.ai_summary
The Ministry of National Defense's 107th Commando Division seeks to procure assorted stationery and training materials (Lot 1), cleaning supplies (Lot 2), and patient recovery items (Lot 3). Bidders must have a valid business license, registration certificate, TIN, VAT certificate, and proof of tax payment.
